November 3, 2020

አማራ ሚዲያ ማዕከል / Amara Media Center

የአሜሪካ ኤምባሲ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ውስጥ ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ በብዙ ንፁሀን ዜጎች ላይ በብሄራቸው ምክንያት በደረሰው አሰቃቂ ግድያ መደንገጡንና እጅግ ማዘኑን ገለፀ።አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋየአሜሪካ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ዛሬ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በኦሮሚያ ምዕራብ ወለጋ ዞን ውስጥ ሴቶችን እና ህፃናትን ጨምሮ ብዙ ንፁሀን ዜጎች ላይ በደረሰው አሰቃቂ ግድያ ኤምባሲው ደንግጧል እና እጅግም አዝኗል ነው ያለው፡፡ ብዙዎቹ ተጎጂዎች በብሄራቸው ምክንያት ጥቃት እንደተፈፀመባቸው በመጠቆም እጅግ በጣም ተጨንቀናልም ብሏል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ዘግናኝ ጥቃት ላይ ግልፅና ጥልቅ ምርመራን በፍጥነት እንዲያካሂድ ፣ በህግ አግባብ መሰረት አጥፊዎችን ለህግ እንዲያቀርብ እና በእነዚህ አካባቢዎች እና በሌሎችም አካባቢዎች የሚገኙ ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ ሁሉንም አስፈላጊ እርምጃዎችን በፍጥነት እንዲያቋቋም እንጠይቃለን ብሏል፡፡በንፁሃን ተጎጂዎች በደረሰው አሰቃቂ ሀዘን ሁሉንም ኢትዮጵያውያን እና አለም አቀፉን ማህበረሰብ በመቀላቀል ለቅርብ ዘመዶቻቸው ጥልቅ ሀዘናችንን እናቀርባለን፤ እናም በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ሙሉ እና ፈጣን ማገገም እንዲገጥማቸው ተስፋ እናደርጋለን ሲል ተመኝቷል፡፡ እያዘንን ሳለን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሰላም ተሰባስቦ ጥላቻን እና ማንኛውንም የኃይል መባባስ እንዲቃወም እናበረታታለን ሲልም አሳስቧል፡፡