November 4, 2020 – Konjit Sitotaw

ትግራይ ( UPDATE )

ሱዳን በትግራይ ክልል ጋር የሚያገናኛትን ድንበር ዘግታለች።

ጠገዴ አዳይጦ በተባለ ቦታ ሰፍሮ የነበረው የወንበዴው ቡድን፣ በዳንሻ በኩል ጥቃት ቢፈጽምም በመልሶ ማጥቃት ድባቅ ተመቷል። ኃይሉ የተዳከመበትና የተበታተነበት ትሕነግ ባእከር ላይ እየተሰራ ካለው እንዲስተሪ ፓርክ ያሰፈረውን ኃይል ወደ ዳንሻ አካባቢ ቢያንቀሳቅስም መለሶ ተደምስሷል።

አዳይጦ፣ ሶሮቃና ቅራቅር ላይ ድል የነሳችሁ የአማራ ልዩ ኃይል ጓዶች! የመከላከያ ሠራዊታችንን ከከበባ በማውጣት፣ ከባድ መሳሪያዎችንም ወደ ዋናው ቤዝ ማስፈር የተቻለው በልዩ ኃይላችንና በሕዝባዊ ሚሊሻው ተጋድሎ። ይህ እጅግ የሚያኮራ ተግባር ነው። መከላከያ ሠራዊትን ከከበባ መታደግ የቻለ፣ ከባባድ የጦር መሳሪያዎችን ከከበባ ማውጣት የቻለ ኃይል ልዩና ሕዝባዊ ሚሊሻ ስላለን ክብር ይሰማናል።

አሸባሪው ትህነግ በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ የነበሩ 2 የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ለመጥለፍ ሙከራ አድርጎ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። አውሮፕላኖቹን ለመጥለፍ ትሕነግ የከፈተው ተኩስ በመከላከያ ሠራዊት መቀልበሱ ታውቋል። አውሮፕላኖቹ አሁን እንደገና አርፈዋል።

በዳንሻ በኩል ወደአማራ ክልል ለማጥቃት ከመጣው የአሸባሪው የትህነግ ሰራዊት በርካታ መሳርያ ተማርኳል። ወልቃይት ጠገዴ አካባቢ በተለያየ ዕዝ ያለ በርካታ የአሸባሪው ሰራዊት በመኖሩ የፌደራሉ ፀጥታ ኃይል ጠንካር ያለ እርምጃ ሊወስድ ይገባል። በተለይ በቀራቅር በኩል በተደጋጋሚ የማጥቃት ሙከራ ማድረጉ ተገልፆአል።

ራያቆቦ ከማንኛውም ተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ ነፃ ስትሆን የክልሉ ልዩ ሀይል ጮቢ በር ላይ በተጠንቀቅ መቆሙንና በትግራይና በአማራ ክልል አዋሳኝ ቦታ ዋጃ ኬላ ላይ ሰፍሮ የነበረው የትግራይ ክልል ልዩ ሀይል አካባቢውን ለቆ መውጣቱን በስፍራው የሚገኙ የአይን እማኞች ገልፀዋል:: የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት ሰራዊቱን ወደ ደንበር አስጠግቶ ሁኔታዎችን በንቃት እየተከታተለ ነው። ትህነግ/ህወሓት ዳንሻ ከተማ ውስጥ ለሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች መሳሪያ እያከፋፈለ ነው። ይህ በመላው ወልቃይት ጠገዴ እየሰሩበት ያለው ጉዳይ ሲሆን የዳንሻው ግን አሁን በዚሁ ቅፅበት እያደሏቸው ነው ተብሏል። ብዛት ያላቸው የቆሰሉ የትግራይ ልዩኃይሎች ወደ ከተማ ንጉስ ሆስፒታልና ወደ መዓረግ ሆስፒታል እየገቡ ነው። በቀጥታ ወደ ትግራይም እየተጫኑ ያሉ አሉ። ምናልባት የሞቱ ሊሆኑ ይችላሉ ቀጥታ ወደ ትግራይ የሚወስዷቸው። በምስኪኑ የጠገዴ ህዝብ ላይ ህወሀት ከባድ መሳሪያ እየተኮሰች ትገኛለች ።አሁን ላይ ቅራቅር ከባድ ውጊያ ከባድ ውጥረት ላይ ትገኛለ ። እናቶችና ህፃናት አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ጫቃ እየተሰደዱ ነው ።የፌድራል ፣የክልልና የዞን የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ለዚህ ሰላማዊ ህዝብ ፈጥነው ሊደርሱለት ይገባል። ትላንት ማታ የተቋረጠው ኔትወርክ ተለቋል። ማታ የተጀመረው ተኩስም እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ቀጥሏል። ተኩሱ እረፍት የለውም። አሁን በዳንሻ ካዛ ወንዝ አከባቢ ከባድ ተኩስ እየተደረገ ነው። መከላከያ ሰራዊት በትግራይ አንዳንድ ተቋማትን ተቆጣጥሯል እየተባለ ነው። ከቀራቅር ያፈገፈገው የትህነግ ኃይል አቅጣጫውን ቀይሮ አሁን ሁለተኛ ዙር ተኩሱን ጀምሮታል። የቀራቅር ከተማ ህዝብ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ከተማውንም ከበባ ውስጥ ሊከቱት ስለሚችሉ ጥንቃቄ ይደረግ።
 ጦርነቱ ወደ አማራ “ክልል” ቀራቅር ከተማ ገብቷል። ትህነግ በጠገዴ ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል። በጠገዴ ቅራቅር በኩል ያለው ተኩስ እንደቀጠለ ነው።ትህነግ/ህወሓት በወልቃይት ጠገዴ ላለፉት ሁለት ዓመት የአማራ አዋሳኝ በሆኑ አከባቢዎች ሲቆፍራቸው በነበሩት ምሽጎች ውስጥ ልዩኃይሎችን አስገብቷል። ሁሉም ወደ ወልቃይት ጠገዴ መግቢያ በሮች በታጣቂዎቹ ለመዝጋት ሞክሯል።

ይህ ጦርነት ለሚቀጥሉት መቶ ዓመታት የምንኖርበትን አገራዊ ይዘት የሚቀይር መሆኑን እያሰብን ማድረግ ያለብንን ሁሉ እያደረግን ነው። ከሃዲያኑ አይቀጡ ቅጣት እየተቀጡ ነው!~ይህ ጦርነት ለምስራቅ አፍሪቃ ቀጣና አደገኛ በሆነው አሸባሪው የትሕነግ ቡድን እና ሀገረ-መንግሥቱን ለመታደግ በተሰለፈው ሠራዊት መካከል የሚካሄድ እንጅ፣ የሕዝብ ለሕዝብ ጦርነት አይደለም! በፍጹም ሊሆንም አይችልም። ወንድም ከሆነው የትግራይ ሕዝብ ጋር ከትሕነግ መደምሰስ በኋላ ሠላማዊ አብሮነታችን ይቀጥላል።~