ተመድ በኢትዮጵያ የሚፈፀሙ ማህበረሰብ ተኮር ጥቃቶች እንዳሳሰበው ገለፀ

ህዳር 04, 2020

ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ

ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ

ዋሺንግተን ዲሲ — የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ በኢትዮጵያ ስለሚፈጸሙ ማህበረሰብ ተኮር ሁከቶችና በሲቪሎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች በቅርብ ቀናት እየወጡ ያሉት ሪፖርቶች በጥልቅ እንዳሳሰቧቸው አስታወቁ።

በጥቃቶቹ ብዛት ያላቸው ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ዋና ፀሃፊው ትናንት ባወጡት መግለጫ ጠቅሰው ለተገደሉት ሰዎች ቤተሰቦች ጥልቅ ሃዘኔን እገልጻለሁ ብለዋል። የጥቃቱ አድራሾች ለፍርድ እንዲቀርቡም ዋና ፀሃፊው ጨምረው አሳስበዋል።

አስከትለውም ሁሉም የሚመለከታቸው ወገኖች በአስቸኳይ ውጥረቱን የሚያረግቡ ርምጃዎች እንዲወስዱ እና ያሉ ተግዳሮቶች አሳታፊ እና ሰላማዊ በሆነ ንግግር መፍትሄ እንዲፈለግላቸው የተመዱ ዋና ፀሃፊ ተማጽነዋል።

4 November 2020

Image result for United Nation logo

The following statement was issued today by the Spokesman for UN Secretary-General António Guterres:

The Secretary-General expresses his alarm over the reported armed clashes in the Tigray region of Ethiopia and calls for immediate measures to de-escalate tensions and ensure a peaceful resolution to the dispute.  He underlines the importance of the stability of Ethiopia for the Horn of Africa region.

The Secretary-General renews the commitment of the United Nations, with its partners in the region, to support the Government of Ethiopia in its reform efforts aimed at building a peaceful and secure future for all its peoples.