November 6, 2020

ዛሬ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን መግለጫ ሰጥቷል።

ፌዴራል ፖሊስ በትግራይ ክልል በሚጠብቀው 22 ተቋማት ላይ ህወሓት ጥቃት እንደፈፀመበት ገልጿል።

የተቋማት ጠባቂዎችን ከማጥቃት ጀምሮ ዝርፊያ መፈፀሙን አሳውቋል።

ጥቃት የተፈፀመባቸው የፌዴራል ፖሊስ አባላት አሁን ላይ ከሰሜን ዕዝ ጋር ሆነው የህግ ማስከበር ስራ እየሰሩ ናቸው ብሏል።

የፖሊስ አባላቱ ከተፈፀመው ጥቃት እንዲያመልጡ የትግራይ ክልል ህዝብ ከለላ ከመስጠት ጀምሮ ጥበቃ ሲያደርግላቸው ነበር።

ከዚህም በተጨማሪ “ህወሓት” በተለያዩ በትልልቅ ከተሞች በተለይ ዋና ዋና ከተሞች “የሽብር ጥቃት” ሊፈፅም የሚችል ኃይል ማሰማራቱን አረጋግጠናል ብሏል።

ከፊሎቹ ተይዘዋል ፤ ከፊሎች ደግሞ እየታደኑ ይገኛሉ ሲል ፖሊስ ገልጿል።