November 6, 2020

የመከላከያ ሰራዊት ትናንት አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ ቀበሌው እንደገቡ ነው የተገለጸው።

ESAT : በምስራቅ ወለጋ ዞን ኬራሞ ወረዳ ባጃን ቀበሌ ሰጊ በተባለ ስፍራ በርካታ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በአማራ ተወላጆች ላይ ዛሬ ማምሻውን ተኩስ ከፍተው በሰው እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።–አርሶ አደሩ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችን ለመመከት ጥረት እያደረገ ቢሆንም የመንግስት ታጣቂዎች በአስቸኳይ ካልደረሱ የከፋ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል ለጣቢያችን እየገለጹ ነው።

ነዋሪዎቹ አክለውም የመከላከያ ሰራዊት ትናንት ጥቅምት 26 / 2013 ዓ/ም አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ ቀበሌው እንደገቡ ነው የተገለጸው።

እስካሁን ግን በጥቃቱ ምን ያህል የሰው ህይወት እንደጠፋ እና ምን ያህል እንደቆሰለ የታወቀ ነገር የለም ።

ዘገባው የሪፖርተራችን ጎበዜ ሲሳይ ነው

ESAT