ከ 7 ሰአት በፊት

አቶ ተመስገን ጥሩነህ [በስተቀኝ]፤ ጄኔራል አደም መሐመድ [በስተግራ]
የምስሉ መግለጫ, አቶ ተመስገን ጥሩነህ [በስተቀኝ]፤ ጄኔራል አደም መሐመድ [በስተግራ]

የአማራ ክልል ፕሬዝደንት የሆኑት አቶ ተስመገን ጥሩነህ ለክልሉ ምክር ቤት የሥልጣን መልቀቂያ ማስገባታቸውን የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ዘገባው እንደሚጠቁመው ፕሬዝደንቱ ለሌላ የሥራ ኃላፊነት በመታጨታቸው ነው መልቀቂያ ያስገቡት።

አቶ ተመስገን ጥሩነህ የሥልጣን መልቀቂያ ያስገቡት በክልሉ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን በሚያካሂድበት ወቅት መሆኑም ተጠቁሟል።

‘ሀገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር በተሠጣቸው ተልእኮ ምክንያት ጥያቄውን ያቀረቡት ርእሰ መስተዳድሩ ፓርቲያቸው በተሠለፈበት ሀገርን የማዳን ስራ ላይ የሚጠበቅባቸውን ለማበርከት ስምሪቱን መቀበላቸውን ለምክር ቤት አባላት ገልፀዋል’ ሲል ኢቢሲ አስነብቧል።

የምክር ቤቱ አባላት በመልቀቂያ ደብዳቤው ዙሪያ ከተወያዩ በኋላ የአቶ ጥሩነህን ጥያቄ መቀበላቸው ተነግሯል።

ምክር ቤቱ በምትካቸው አቶ አገኘሁ ተሻገርን ለርዕሰ መስተዳድር በእጩነት እንዳቀረቡ ዘገባዎች ጠቁመዋል።

አቶ ተመስገን ጥሩነህ የቀድሞውን የአማራ ክልል ፕሬዝደንት አምባቸው መኮንን [ዶ/ር] በመተካት ነበር የተሾሙት።

በሌላ በኩል ጠ/ሚ ዛሬ ጠዋት አዳዲስ ሹመቶች ማፅደቃቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ አስታውቋል። በዚህም መሠረት፡

እንዲሁም ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.መ ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን የጠቅላይ ሚንስትሩ የብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ሚንስትር አድርገው ሾመዋል።