መነሻ ገጽ
በትግራይ ክልል የሚገኙ ሁሉም ባንኮች እንዲዘጉ ብሔራዊ ባንክ ወሰነ

8 November 2020

በጋዜጣዉ ሪፓርተር

ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ በትግራይ ክልል በሚገኙ ባንኮች ላይ የዘረፋ ምልክቶች በመታየቱ በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ባንኮች ተዘግተው እንዲቆዩ መወሰኑን አስታወቀ።

በትግራይ ክልል 616 የሚሆኑ የሁሉም ባንኮች ቅርንጫፎች መኖራቸውን ያስታወሰው ብሔራዊ ባንክ ፤ በበንኮች ላይ የተስተዋለው የዘረፋ ሙከራ ተገቢ ያልሆነ እና በባንኮቹ የቆጠቡ የክልሉ ነዋሪዎችን ሀብት መዝረፍ በመሆኑ ከተጠያቂነት ማምለጥ አይቻልም ብሏል።