ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ግጭት ውስጥ የሚገኘው ህወሓት ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ጥቃቱን መፈጸማቸውን ለትግራይ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ጌታቸው ረዳ አሁን ለDW international በትግርኛ እየሰጠ ባለው መግለጫ ጎንደርና ባሕርዳርን ሌሊት በሚሳኤል እንደደበደቡ ገልጿል።
የጉዳት መጠኑንም ሲጠቅስ ባሕር ዳር ላይ ወታደራዊ ተርሚናል፣ ጎንደር ላይ ወታደሮችን መትተናል ይላል። ቀጣይም የትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ (ከኤርትራ አስመራን ጨምሮ) በተመረጡ ቦታዎች ላይ እንመታለን ሲል ዝቷል።
በራያ ላይ እየተደበደብንም ሲልም አክሏል። የአማራ ሕዝብ በሰላም እንዲኖር ከፈለገ የጥፋት ኃይሉን ከመደገፍ ይቆጠብ ሲል ሰማሁት። ሚሳኤል አማራ ክልልና ኤርትራ ላይ እንተኩሳለን ! ዝም ብለን አንቀመጥም ! ሲል ዝቷል።