November 13, 2020DW Amharic

የተባበሩት መንግሥታት ቃል-አቀባይ ሩፐር ኮልቪሌ የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ዘገባን ተከትሎ ለዶቼቬለ ለዶቼ ቬለ እንደገለጹት የማይካድራዉን ወንጀል የጦር ወንጀል ብሎ ለመፈረጅ ማጣራት ያስፈልጋል።

UN-Sprecher Syrien Friedensgespräche Rupert Colville (United Nations Geneva/Jean-Marc Ferré)

የተባበሩት መንግሥታት ቃል-አቀባይ ሩፐር ኮልቪሌ የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ዘገባን ተከትሎ ለዶቼቬለ ለዶቼ ቬለ እንደገለጹት የማይካድራዉን ወንጀል የጦር ወንጀል ብሎ ለመፈረጅ ማጣራት ያስፈልጋል። « አምነስቲ ኢንተርናሽናል ስለጅምላ ጭፍጨፋው ያወጣው ዝርዝር ዘገባ በደቡብ ምዕራብ ትግራይ ማይካድራ ላይ ተፈጸመ የተባለው ግድያ ሙሉ ለሙሉ ገና ባለመረጋገጡ፤ ከፍተኛው ኮሚሽን ሙሉ ማጣራት እንዲካሄድ ጥሪ ያቀርባል። በአሁኑ ውጊያ ተሳታፊዎች ሆን ተብሎ የተደረገ ከሆነ ሲቪሎች ላይ የተፈጸመው ጅምላ ግድያ የጦር ወንጀል ነዉ። ነገር ግን የሆነዉን ነገር ለማወቅና ተጠያቂነት እንዲኖር  በገለልተኛ ወገን መጣራት ይኖርበታል።  

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ