ራያ ዋጃና ጥሙጋ ቆቦ ወ አዘቦ ጨርጨር መሆኒ እና ባላ ከእልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ በሁዋላ የባርነት ቀንበራቸው ተሰብሯል:: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አላማጣንና ኮረምን ከህወሀት ሰራዊት ነፃ አድርጎ ግስጋሴውን ቀጥሏል:: በሐገር መከላከያ ሰራዊት፣በአማራ ልዩ ሀይልና በሚሊሻ አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

(አብመድ) የሐገር መከላከያ ሰራዊትና የአማራ ልዩ ሀይል የተለያዩ አካባቢዎችን በድል አልፈው ነው ከዘራፊው የትህነግ ልዩ ኃይል ነጻ ያደረጉት።
– የሐገር መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ልዩ ኃይል በራያ ግንባር ከባድ ጥቃት ሰንዝረዋል። የትህነግ ስግብግቡ ጁንታ ልዩ ኃይል እየተደመሰሰ ነው፤ጉዳትም ደርሶበታል፤ አካባቢውንም ለቆ እየፈረጠጠ ነው።
–
የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉት ትህነግ እያራመደ ባለው አምባገነናዊ ስርዓት ግፍ ደርሶባቸዋል።
–
አሁን ላይ በመከላከያ ሰራዊት፣ በአማራ ልዩ ኃይልና በሚሊሻ አባላት ከትህነግ ከሐዲ ቡድን ነጻ በመውጣታቸው ደስታቸውን እየገለጹ ነው።
–
የትግራይ ህዝብ የዘራፊውን ትህነግ ቡድን ሐገርን የማፍረስ ተግባር በመቃወም ከመንግስት ጎን መቆም እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
–

