የህወሓት ጦር ራያ አላማጣ ላይ በደረሰበት ጥቃት ተሸንፎ ከአካባቢው ሲባረር በእስር ላይ የነበሩ 10 ሽህ ያህል ሰዎችን ይዞ መሸሸቱ ተገለፀ።

ህዳር 6 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋየአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ባወጣው መግለጫ ሕወሓት በመከላከያ ሰራዊት በደረሰበት ጥቃት የራያ የአላማጣ ከተማን በሽንፈት ለቆ መውጣቱን አስታውቋል።ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በላይ የሆኑ በርካታ የራያ አላማጣ አካባቢው ወጣቶችም በሽብር ተግባር በተሰማራው በሕወሓት ኃይል ለጦርነት እንመለመላለን በሚል ስጋት ከአካባቢውን ለቀው መሰደዳቸውን ስለመናገራቸው ተገልጧል።ህወሓት ከራያ አላማጣ በደረሰበት ጥቃት ተሸንፎ ሲባረርም በእስር ላይ የነበሩ 10 ሽህ ያህል ሰዎችን ይዞ መሸሸቱ ተገልጧል።አላማጣን በቁጥጥር ስር ሲውልም የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራው በሰላማዊ ዜጎች ላይ ተጽዕኖ እንዳያስከትል አስፈላጊው ጥንቃቄ ታክሎበት፣በውጤታማ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ያሳያል ሲል በመግለጫው ተወስቷል።በራያ ዋጃ እና ጥሙጋ በትናንትናው እለት በመከላከያ ሰራዊትና በአማራ ልዩ ሀይል፣በፋኖዎችና በሚሊሻዎች የአብሮነት ትግል ከካሀዲው የሕወሓት ቡድን ነጻ መውጣታቸው አብመድን ጨምሮ በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት መዘገቡ ይታወሳል።