November 14, 2020

ምሁር ማለት እንደ  ገብረመድህን አርዓያ፣ ነጋሲ በየነ፣ ጌታቸው ረዳ(ኢትዮጵያ ሠማይ) የረጅም ጊዜ ትግላችሁ ተሳክቷል፡፡

‹‹መቼም የትም አይደገም!›› “Never and Ever again”

የትግራዋይ ምሁራን በፅናትና በቆራጥነት ግፍነን በመታገል ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ቆማችሁ እውነቱን ለህዝብ በማሳወቃችሁ ትሪክ ሲያስታውሳችሁ ይኖራል፡፡ ገብረመድህን አርዓያ፣ ነጋሲ በየነ፣ ጌታቸው ረዳ(ኢትዮጵያ ሠማይ) የረጅም ጊዜ ትግላችሁ ተሳክቷል፣ በወደቁት ሠማዕታት ስም ምስጋና ይገባችኃል፡፡ ዛሬ የወያኔ አራጆችን አስወግደናል፣ነገ ደግሞ የኦነግ አራጆችን (ጆኖሳይድ) ድባቅ እንመታለን! ብዙ የህዝብ ልጆች በአንድ መቃብር ሥፍራ በህብረት በአንድነት ተቀብረዋል፤ ድብቁ የጅምላ መቃብር በተለያዩ ክልሎች ውስጥ ይገኛሉ፣ ይፋ እንዲሆን በጋራ መታገል ታሪካዊ ኃላፊነታችን ይሆናል፡፡ በኢትዮጵያ ግድያ፣ እስራትና ሰደት ‹‹መቼም የትም አይደገም!›› “Nevere and Ever again”ብለን ቃል ኪዳን በመግባት ከስህተታችን ተምረንና ችግራችንን በጠረጴዛ ዙሪያ ብቻ በመፍታት፤ ለቀጣዩ ትውልድ ሃገራችንን በፍቅርና በአንድነት ማስቀጠል ኃላፊነት አለብን እንላለን፡፡

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)የትግራይን ህዝብ ከ1975እኤአ እስከ 2020እኤአ ለአርባ ስድስት አመታት በግፍ ገዝተውታል፡፡ በዚያ ዘመን የመጀመሪያዎቹን የህወሓት መሪዎች የነበሩትን በግፍ ከገደሎቸው የትግራይ ልጆች ውስጥ ገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ መሃሪ ተክሌ፣ አጽብሃ ዳኛው፣ ዶክተር አታክልት ቀጸላ ደም ደመ ከልብ ሆኖ አልቀረም፤ እውነተኛ ታሪካቸው ይዘከራል፡፡ ህወሓት ኢህአዴግ ለአለፉት ሃያ ሰባት አመታት የኢትዮጵያን ህዝብ በአንባገነንነት በግፍ አገዛዝ አስተዳድሮል፣ ብዙ ሽህ ሰዎች ገድሎል፣ አስሮል አሰድዶል፡፡

አንድ የትግራይ ተወላጅ ምሁር በአንድ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግርመጠረት ወያኔ ይሄን ለምን እንደማይቀበለው እንገንዘብ፤የህወሓት/ማሌሊት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው ሌላ አማራጭ መንገድ የማያውቁ በስታሊናዊ ጨካኝ አስተሳሰብ ተኰትኩተውና እንደ ዓሳራ ግመል ፊታቸውን ተሸብበው ያደጉ ናቸው:: መለስ ዜናዊም ብልጥ ነው:: ሆን ብሎ የህወሓት/ማሌሊት ሶፍት ዌር ፕሮግራም በጭንቅላታቸው ውስጥ የገጠመላቸው ስለሆኑ ከዚያ አጥር ወጥተው ሌላ ሰፋ ያለ ዓለምና ሳይንስ የሚያዩበት መነፅር የላቸውም:: ቢተኩሱም! ቢነግሱም! ቢማሩም ያው ናቸው ምንም አይለወጡም:: ቀደም ብሎ በአእምሮኣቸው ከተገጠመላቸው የሶፍት ዌር ፕሮግራም ውጭ ሌላ የሚያውቁትና የሚናገሩት ሰላማዊ ቋንቋ የላቸውም:: ሁሉ ጊዜአካኪ ዘራፍ!! በለው ደምስሰው!! – ያዘው ልቀቀውየሚሉትን ቃላቶች ብቻ ናቸው በአእምሮኣቸው የሚታዩባቸው:: ሕግ አይገዛቸው! ባህል አይገዛቸው! ታሪክ አይገዛቸው! ሀይማኖት አይገዛቸው! ጊዜ አይለውጣቸው! ዕድሜያቸው ልክ አንድ ዓይነት መዝሙር እየዘመሩ ጭንቅላታቸውን በማሌሊታዊ ሰይጣናዊ አስተሳሰብ እንደተቆለፈ ያልፋሉ:: በመሆኑም አሁን እየታየ ያለው ትልቁ አሳሳቢ ጉዳይ የህወሓት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው በማሌሊት ሶፍት ዌር ፕሮግራም መደንዘዛቸው ብቻ አይደለም ችግሩ:: ነገር ግን ከጫካ ይዘውት የመጡት መድሃኒት አልባ በሽታ ወደ ሌሎች ክልሎችም በፈጣን ሁኔታ እየተዛመተ መምጣቱ ነው:: ስለዚህቤቱን ሳይቃጠል በቅጠልእንደተባለው እኛም በተራችን ሳንታመም የመከላል ዘዴ መፍጠር ይኖርብናል፡፡

የወያኔ የጦር አበጋዞች መንግስት የፖለቲካ ሥልጣናቸውን በሰላማዊ መንግድ ያሸጋግራሉ ብሎ መጠበቅ ከእባብ እንቁላል እርግብ ይፈለፈላል ብሎ እንደመተበቅ ይቆጠራል፡፡ ህወኃት በ46 ዓመታት የፈጸማቸው ወንጀሎች ተቆጥረውና ተዘርዝረው አይዘለቁም::

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ሕገ-መንግሥትና አስሩ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥቶች ህገ-መንግሥት በስብዕና ላይ ስለሚፈጸም ወንጀሎች፣ በይርጋ አይታገድም!!! በምህረት ወይም በይቅርታ አይታለፍም!!!  ስለዚህ የሰው ዘር የማጥፋት፣ ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ የመውሰድ፣ በአስገዳጅነት ሰውን የመሰወር ወይም ኢሰብዓዊ የድብደባ ድርጊቶችን በፈጸሙ ሰዎች ላይ ክስ ለማቅረብ አስፈላጊውን መረጃዎች በማስቀመጥና በማከማቸት ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረብ እንደሚቻል ተረድቶ የሕገአራዊት ዘመንን ወደ ህገሰው ዘመን ማሻገር እንደ ሰው የሚያስቡ ዜጎች በዘርና ኃይማኖት ፍጅት ጠንሳሽ የመንጋና ጅምላ ቡድኖችን ለህግ የማቅረብ ኃላፊነት አለባቸው እንላለን፡፡

በኢትዮጵያ ድብቁ የወያኔና ኦነግ የዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጆኖሳይድ) ቀጥሎል ድብቁ የጅምላ መቃብር ተቆፍሮ እንዲወጣ ህዝብ ያላሰለሰ ትግል ማድረግ ይገባዋል፡፡ በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ግንባር (ህወሓት) እና በኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ)በግፍ የተፈፀመው በተለያዩ ክልሎች  ትግራይ፣ አማራ፣ ፣ኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ሱማሌ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በድብቅ የተፈፀሙ ግድያዎች እና ድብቅ የጅምላ መቃብሮች ተጋልጠው መውጣት አላባቸው እንላለን፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ሕገ-መንግሥትና አስሩ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥቶች ህገ-መንግሥት በስብዕና ላይ ስለሚፈጸም ወንጀሎች፣ በይርጋ አይታገድም!!! በምህረት ወይም በይቅርታ አይታለፍም!!!

https://www.Youtube.com/watch?v=E6UEc9WizBs/ ESAT human right eyewitness testimony the massacre of Bedeno 1992 Ethiopia

https://www.Youtube.com/watch?v=EcZJIFUKx9M/Aug 25,2016

አንድ ሚሊዮን የኦሮሞ ህዝብ ከሱማሌ ክልል ተፈናቅለዋል!!! ግማሽ ሚሊዮን የአማራ ህዝብ ከተለያዮ ክልሎች ተፈናቅለዋል!!! በደቡብ ክልል 450 ሽህ ጌዲዬ ህዝብ ተፈናቅለዋል!!! የወያኔ መንግሥት የከፋፍለህ ግዛ ዘመን አብቅቶል!!! የወያኔ የኮንትሮባንድ ንግድ ሲባል ህዝብ አይፈናቀልም!!! ኤርትራን ያስገነጠለ፣ የባህር በር ሃገሪቱን ያሳጣ፣ ባድሜን አሳልፎ የሸጠ የወያኔ ሥርዓት በኢትዮጵያዊ ትግራይ ወጣቶች ትግል ይገረሰሳል!!! በቃ ፍየል ሲሰባ፣ ሾተል ይልሳል!!!  ሰው ታሞ እንጅ፣ ፈርቶ አይሞትም! የተፃፈልንን እኖራለን!!! ህዝባዊ ዲሞክራሲዊ ጋርድ ሆነን ለሃገራችን ዘብ እንቁም፡፡ ወያኔ ታግለን የያዝነውን የፖለቲካ ሥልጣን አናስነጥቅም፣ በማለት የትግራይን ህዝብ በስብኣዊ ጋሻነት ይዞል፡፡ የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ወንድሞቹና እህቶቹ ጎን ቆሞ ወያኔን የሚፋለምበት ጊዜ አሁን ነው እንላለን፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በሚኖሩ ዜጎች በተለይም በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ትኩረት ተሠጥቶት ወንጀለኞቹ ለፍርድ ቀርበው አስቸኮይ እርምጃ ለወሰድባቸው ይገባል እንላለን፡፡ የኦሮሞ ድርጅቶች ኦነግ፣ ኦነግ ሸኔ፣ ኦፌኮ ወዘተ በኦሮመያ ክልል ውስጥ አንዱን ነዋሪ አንዱን ሠፋሪና መጤ

ሠላም ለኢትዮጵያ!!

ፍርድ ለህወኃት ደም መጣጮች፡፡

ፍየል ሲሰባ፣ ሾተል ይልሳል!!!

ደውሉ የሚደወለው ለማን ነውFor Whom The Bell Tolls?

የትናንቱ ውጊያ ከኮረብታው ላይ፣ ሲያውድ የባሩድ ሽታ፣

በዛ ቅዝቃዜ! ሆድ ሲንቦጫቦጭ፣ ሙቀት በብርድ ሲረታ፣

የጠመንጃ ጩኸት፣ የተኩስ እሩምታ ሰማየ ሰማያቱን ሲነድለው

በዛ ውጊያ የጦር ጀነራሎቹ ትክክል ነበሩ …ማን አለና?

ለባድማ መሬት ብሎ ሰው ይሞታል፣ ግን ለምን? እነሱም አያውቁማ!!!

ያመረቀዘ ቁስላችን፣ ለእነሱ ክብርና ኩራት ሆናቸው!!!

በባድማ! ያ ሁሉ የደሃ ልጅ ረግፎ፣ የአምስቱ የጦር መኮንኖቹ  ሲሳይ፣

በሹመት ላይ ሹመት፣ በሜዳልያ ላይ ሜዳልያ፣ በበላይ ላይ በላይ፣

የእብደትና ህመም ደዌችንን፣ በእርግጥ ያውቃሉ ያሳለፉነውን ስቃይ፣

ታዲያ! ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?

ጊዜው እንደ ወንዝ እየገዘፈ፣ እንደ አውሎ ንፋስ እየከነፈ፣ ነፍስ ነፍስን ካጠፋ፣

የባህር ማዶ ቄጤማ፣ ሲወድቅ ሲነሳ በተስፋ

ታዲያ ደውሉ የሚያቃጭለው ለማን ነው? ኩኩሉ ሳይል አውራ ዶሮው፣

የደሃ ልጅ የሆናችሁ፣የእናንተን ዕጣ ፈንታ ልንገራችሁ፣

ከመሞታችሁ በፊት፣ ቀኑን ተሠናበቱ፣ ሰማየ ሰማያቱን እያያችሁ፣

በመጨረሻ እስትንፋሳችሁ፣ ትሁን ንዛዜችሁ ለእናታችሁ!!!

ነፍሳችሁ ስታርግ፣ ትሰወራለች ቀስ ብላ ጥላችሁ፣

በድቅድቁ ጨለማ፣ በነጎድጎዳማ መብረቅ ሲርድ ሰማይ፣

ለተቀጨ ዓላማችሁ ብካይ፣ አጎሩ ለረገፈ መንፈሳችሁ ታላቅ ራዕይ፣

ነፍስ ረቂቅ ሚስጢር፣ እንግዳ ነገር ሆነች ዐይናችሁ ላይ፣

ፀጥታው ባርቆ ይሰማል፣ በዝምታ አድምጥ የልብህ ትርታ ካንተ ስትለይ፣

የብርሃን ጨረር ፈንጥቃ ለስንብት፣ በዚህ ዓለም ከተስፋ ሌላ አረ ምን ሊታይ?

ሞታችሁን ባናይ እንኮን፣ ያዩት ይመሰክሩ የሌት ጨረቃ የቀን ፀሃይ

የዓይነ ስውር ዓይን ሲበራ፣ ሞት በህይወት ልትረታ ትንሳኤ ላይ፣

ታዲያ እማማ፣ ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?

ጊዜው እንደ ወንዝ እየገዘፈ፣ እንደ አውሎ ንፋስ እየከነፈ፣ ነፍስ ነፍስን ከገፋ፣

የባህር ማዶ ቄጤማ፣ ሲወድቅ ሲነሳ በተስፋ

ድህነትና ርሃብ፣ በሽታና ሰደት ሳናጠፋ

በቌንቌ ተካለን፣ ማኛ ጤፍ ዘር ስንነፋ

ጦርነት አርግዘን ስናናፋ፣ ድንቁርናችን ምነው ከፋ

ዛሬም ወገን በወገን ላይ፣ በዘር ጦር ሰብቀን ስንነሳ፣

የባደማ ፆረና ሞት አልፈን፣ በወልቃይት፣ራያና አፋር ጦር ሜዳ ደንገላሳ፣

ታዲያ እማዬ ደውሉ የሚደወለው ለእኛ ሞቾች ነው?  ትንቢተ ትንሣዔ ራቀ ምነው?

ጦርነት ‹መቼም የትም አይደገም!!!› ሳንል! መፈናቀላችን ስለምን ነው! ሰደቱንስ መች ለመነው?

የሰው ልጅን ከኃጢያቱ እንፈውሰው፣ ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?

ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው? ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?

(ኦክቶበር 10 ቀን 2018 ተፃፈ)