በሠራዊቱ ዝግጁነት እና በሕዝቡ ደጀንነት የተደናገጠው ጽንፈኛው ቡድን አካባቢውን ጥሎ የሸሸ ቢሆንም፣ በአላማጣ ከተማ ታስረው የነበሩ 10 ሺህ ዜጎችን ይዞ ማፈግፈጉን የደቡብ እዝ የሰው ሀብት እና ሚዲያ ሥራዎች አስተባባሪ ኮ/ል ደጀኔ ጸጋዬ ተናግረዋል።
የደቡብ እዝ የሰው ሀብት እና ሚዲያ ሥራዎች አስተባባሪ ኮ/ል ደጀኔ ጸጋዬ
ዋልታ – በራያ ቆቦ እና አካባቢው ሕግን ለማስከበር የተሠማራው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ጋር በመተባባር ዋጃ፣ ጥሙጋ፣ አላማጣ እና አካባቢውን ከጁንታው የሕወሓት ቡድን ነፃ አውጥቶ መቆጣጠሩን ገልጿል። በሠራዊቱ ዝግጁነት እና በሕዝቡ ደጀንነት የተደናገጠው ጽንፈኛው ቡድን አካባቢውን ጥሎ የሸሸ ቢሆንም፣ በአላማጣ ከተማ ታስረው የነበሩ 10 ሺህ ዜጎችን ይዞ ማፈግፈጉን የደቡብ እዝ የሰው ሀብት እና ሚዲያ ሥራዎች አስተባባሪ ኮ/ል ደጀኔ ጸጋዬ ተናግረዋል።–ጽንፈኛው ቡድንን በዜጎች ላይ ጉዳት ሳያደርስ ለመቆጣጠር ሠራዊቱ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተራመደ እንደሚገኝ አብራርተዋል። የአማራ ልዩ ኃይል አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ቢሰጥ ጌታሁን በበኩላቸው፣ ኅብረተሰቡ ሳይጎዳ አካባቢውን ለመቆጣጠር እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በፋሽስታዊው ኃይል የሚደረገው ማጥቃት የቀጠለ ሲሆን፣ ግራካሶ እና ጨርጨር ላይ ያለው የጁንታው ኃይል ከፍተኛ ጥቃት እየፈጸመበትና ኪሳራም እያደረሰበት መሆኑን ረዳት ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡ በቅርብ ሰዓታት እነዚህን አካባቢዎች መቆጣጠር እንደሚቻልም ጠቁመዋል፡፡–
የአማራ ልዩ ኃይል አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ቢሰጥ ጌታሁን
የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ደግሞ ደስታቸውን በጭፈራ እና በተለያዩ መልኩ ሲገልጹ ውለዋል፡፡ ለዋልታ አስተያየታቸውን የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎችም በአካባቢው ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በላይ የሆናቸው ልጆች በሙሉ በግዳጅ ወደ ጦር ሜዳ ሲመለመል ስለነበር ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ከተማውን ለቀው እንደሸሹ ተናግረዋል፡፡–እንዲሁም ለትግራይ ልዩ ኃይል ድጋፍ በሚል ከፍተኛ ገንዘብ እንዲያዋጡ የሚገደዱ ሲሆን፣ ሽሮና በርበሬ ሳይቀር በጉልበት ከየቤቱ ገብተው ስወስዱ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ “ለዓመታት በማንነታችን ምክንያት ከፍተኛ በደልና ግፍ ሲፈጸምብን ቆይተን ዛሬ ነፃ ወጥተናል” ሲሉም ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ለመከላከያ ሰራዊት ሁሉንም ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን የተናገሩት ነዋሪዎቹ ይህ ኃይል ተደምስሶ በወንጀል ላይ የተሳተፉ ሁሉ ለህግ እስኪቀርቡ ድረስ ከመከላከያ ሰራዊት እና ልዩ ኃይል ጋር በጋራ መስራታችንን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡–
የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ደግሞ ደስታቸውን በጭፈራ እና በተለያዩ መልኩ ሲገልጹ ውለዋል፡፡