November 15, 2020

በመላው ዓለም ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን፣ የኢትዮጵያና ኤርትራ ወዳጆች የቀረበ  ታላቅ የትብብር ጥሪ

<<ተቀማጭነታቸው በሰሜን አሜሪካና በአውሮፓ ያደረጉ ሰባት የኢትዮጵያ ሲቪክ ድርጅቶች በጋራ በመሆን የኢትዮጵያ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር፣ የአሸባሪውና የከሃዲውን የህወሃት መሪዎች ወደ ህግ ፊት ለማቅረብ በትግራይ ውስጥ የጀመረውን ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ የአለም አቀፍ ማህበረስብ ትክክለኛውን ግንዛቤ እንዲጨብጥ፣ ብሎም እንዲደግፍ ባለ ሶስት ገጽ ደብዳቤ አሰራጭቶአል። ደብዳቤው ለተባበሩት መንግስታት፣ ለአፍሪካ ህብረት፣ ለአለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት፣ ለልዩ ልዩ አለም አቀፍ ተቋማት እንዲደረስ ተደርጎአል።

(ከታች ያለውን ምስል ይመልከቱ)

ከሰሞኑ የህወሃት/ትነግ የአለም አቀፍ የፕሮፖጋንዳ ማሽነሪ፣ ሌሎች ጽንፈኛ ሃይሎች፣ ኣንዲሁም ባእዳን ጋዜጠኖችና ምሁራን ጋር በማበር በአለም አቀፍ ደረጃ በሚዲያዎች፣ በፓርላማ አባላት፣ በሶሻል ሚድያ የሚደረግ የተቀነባበረ ዘመቻ በኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ያለውን፣ ግጭቱ መቼ፣ ለምን፣ ከምን ተነስቶ ለሚሉ ጉዳዮችን በሚመለከት በርካታ የሃስት ትርክቶች ከማስራጨትም አልፎ “የእርስ በእርስ ጦርነት” እንደሆነ፣ መንግስት ተገዶ የገባበት መሆኑ እውነታው ሆኖ ሳለ “ትግራይን ለመውረር” እንደሚደረግ ለማቅረብ የተሄደበትን ውዥንብሮችና ውሸቶችን ርቀት ለማጥራት በማሰብ ድርጅቶቹ በጋር ስብሰባ በማድረግ የተዘጋጀ ደብዳቤ ነው። የዚህን ደብዳቤ ይዘት መነሻ በማድረግ በምትገኙባቸው ሀገሮች መንግስታት፣ ለጋዜጠኞች፣ ለፓርላማ አባላት፣ ለሲቪክ ተቋማት ፣ በተለይም ጽንፈኞቹና የህወሃት አሸባሪዎች የውጭ ተባባሪዎች ትኩረት ያደረጉባቸውና ፡ የተሳሳተ ግንዛቤ ያላቸውን፣ የተሳሳተ መግለጫ ላወጡ ልዩ ልዩ የመንግስትና ከመንግስት ውጭ የሚገኙ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ፣ እንዲሁም ጋዜጠኖች በማድረስ እንድትተባበሩ ጥሩ እናደርጋለን።>>