November 16, 2020

Image may contain: 2 people, people standing

DW : የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአማራ ክልል በሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎች እና በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን አወገዘ።–የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ክሪስቶፈር ቡርገር ህወሓት “ግጭቱን ለማስፋት እና የጎረቤት አገሮችን ጎትቶ ለማስገባት የሚያደርገው ሙከራ” እጅግ አሳሳቢ ነው ብለዋል።

“ኹኔታው በተለይ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ግጭቱን ለማስፋት እና አጎራባች አገሮችን ጎትቶ ለማስገባት የሚያደርገው ሙከራ ሥጋት የሚፈጥር ነው” ብለዋል ቃል አቀባዩ።

የትግራይ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ሚሳኤል መተኮሱን አረጋግጠው ተጨማሪ ተመሳሳይ ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ባለፈው ቅዳሜ ምሽት በአስመራ ላይ ጥቃት መሰንዘሩ የተሰማው የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና የትግራይ ኃይሎች ኃይለኛ ውጊያ ከጀመሩ በኋላ ነው። የትግራይ ባለሥልጣናት ኤርትራ ከኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት ወግና በግጭቱ ተሳትፋለች የሚል ክስ አቅርበዋል።

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ክሪስቶፈር ቡርገር “በአማራ ክልል በሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎች እና በኤርትራ የተፈጸሙ እና ህወሓት ኃላፊነት የወሰደባቸውን ጥቃቶች አጥብቀን እናወግዛለን። ኹኔታውን ለማረጋጋት እና መፍትሔ ለማበጀት ፖለቲካዊ ሒደት ያስፈልጋል” ሲሉ ዛሬ በበርሊን ከተማ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።