November 17, 2020

34 የሕወሓት የፋይናንስ ተቋማትን ማሳገዱን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ

ሱር ኮንስትራክሽን ፣ ጉና የንግድ ስራዎች ፣ ትራንስ ኢትዮጵያ፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ ፣ ሠላም የህዝብ ማመላለሻ ማህበር ፣ ሜጋ ማተሚያ፣ ኢፈርት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንዲሁም ኢፈርት ኤሌክትሪካል ቢዝነስ እገዳ ከተጣለባቸው ተቋማት መካከል ናቸው፡፡


የኢትዮጵያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግበተለያዩ ወንጀል ተግባራት ውስጥ ስለመሳተፋቸው ምርመራ ለመጀመር የሚያስችል በቂ ማስረጃ የተገኘባቸው ድርጅቶች ሀብቶች ታገዱ

************

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የዘር ተኮር ጥቃት እና የሽብር ድርጊት እንዲፈጸም የገንዘብ ድጋፍ በማቅረብ፣ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ከሚንቀሳቀሰው የትህነት/ ህወሃት ሀይል ጋር ግንኙነት በመፍጠር፤ በመመሳጠር እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የተሳተፉ ስለመሆናቸው እና በግብር ስወራ እና የሙስና ወንጀል ድርጊቶች ውስጥ ስለመሳተፋቸው ምርመራ ለመጀመር የሚያበቃ በቂ ማስረጃ የተገኘባቸውን ከታች ስማቸው የተጠቀሱትን ድርጅቶች የሚንቀሳቀሱ እና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን በባንክ ያለቸውን ገንዘብ ጨምሮ ከህዳር 07 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንዲታገዱ አድርጓል፡፡

እግዱ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ድርጅቶቹ ሀብታቸውን ለማሸሽ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሆኑ በቂ ማስረጃ የቀረበ በመሆኑ ንበረቶቹ ሳይሸሹ ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ውሳኔ እስኪሰጥባቸው ማቆየት ተገቢ መሆኑ ስለታመነበት ነው፡፡–የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል የመመርመር እና ሀብትን የማስመለስ ስራውን እስኪያጠናቅቅ ድረስ የታገዱት ንብረቶች እንዳይጎዱ እና እንዳይባክኑ ጠብቆ የሚያቆይ የንብረት አስተዳዳሪ የሚሾም ሲሆን አስተዳዳሪው ስራውን ተቀብሎ ማስተዳደር እስኪጀምር ድረስ የድርጅቶቹ አስተዳዳሪዎች ንበረቱን በሚገባ የመጠበቅ ኃላፊነት አለባቸው፡፡በቀጣይ የምርመራ እና ክስ ሂደቱን ተከታትለን ለህዝቡ የምናሳውቅ ሆኖ የታገዱት ድርጅቶች ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩት መሆናቸውን እንገልጻለን፡፡1. ሱር ኮንስትራክሽን2. ጉና የንግድ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር3. ትራንስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር4. መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር5. ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አክሲዮን ማህበር6. ሜጋ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር7. ኤፈርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር8. ኤፈርት ኤሌክትሪካል ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር9. ኤፈርት ዲዛይን እና ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር10. ኢዛና ማዕድን ልማት ኃ/የተ/የግ/ማህበር11. ቬሎሲቲ አፖራልዝ ካምፓኒስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር12. መሰቦ ቢውልዲንግ ማቴሪያል ፕሮዳክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር13. ሳባ ዳይሜንሺናል ስቶን ኃ/የተ/የግ/ማህበር14. መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ15. ሼባ ታነሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር16. ኤ.ፒ ኤፍ17. ሜጋ ኔት ኮርፖሬሽን18. እክስፕረስ ትራንዚት ሰርቪስ19. ደሳለኝ ካትሪናሪ20. ሼባ ታነሪ ፋክተሪ አክሲዮን ማህበር21. ህይወት አግሪካልቸር መካናይዜሽን22. ህይወት እርሻ ሜካናይዜሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር23. አልመዳ ጋርመንት ፋክተሪ24. መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ25. ደደቢት ብድርና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር26. አዲስ ፋርማሲቲካልስ ፕሮዳክሽን27. ትግራይ ዴቨሎፕመንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር28. ስታር ፓርማሲቲካልስ ኢፖርተርስ29. ሳባ እምነበረድ አክሲዮን ማህበር30. አድዋ ፍሎር ፋክተሪ31. ትካል እግሪ ምትካል/ ትግራይ/ ት.እ.ም.ት/32. ብሩህ ተስፋ ፕላስቲክ ኃ/የተ/የግ/ማህበር33. ደሳለኝ የእንስሳ መድኃኒት አስመጪና አከፋፋይ ኃ/የተ/የግ/ማህበር34. ማይጨውፓርትክል ቦርድ ፋክተሪ