See the source image

November 17, 2020

Ethiopia: WHO director-general works as TPLF diplomat

Ethiopia accuses Tedros Adhanom of soliciting diplomatic, military support for Tigray People’s Liberation Front

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በህወሀት ቡድን ላይ ህግ የማስከበር ዘመቻ ከጀመረበት ዕለት አንስቶ ዶ/ር ቴውድሮስ ሲያደርጉት የነበረውን እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ መንግስት ጠንቅቆ ያውቃል – አንድ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ኢትዮ ኤፍ ኤም – የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ለህወሀት ቡድን የዲፕሎማሲ ስራ ሲሰሩ እንደነበር ተገለፀ፡፡

ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ለህወሀት ቡድን ዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ ድጋፍ እንዲደረግ የአለም መንግስታትን በመጠየቅ እረገድ ሙሉ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ገልፀዋል፡፡

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ለአናዶሉ ኤጀንሲ እንደተናገሩት የሀገር መከላከያ ሰራዊት በህወሀት ቡድን ላይ ህግ የማስከበር ዘመቻ ከጀመረበት ዕለት አንስቶ ዶ/ር ቴውድሮስ ሲያደርጉት የነበረውን እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ መንግስት ጠንቅቆ ያውቃል ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በህወሃት ላይ የሚወስደውን ወታደራዊ እርምጃ እንዲያስቆሙ እንዲሁም በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲያሳድሩ ሲጠይቁ ነበር ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል፡፡

እንደ አውሮፓውያኑ ከ 2017 ጀምሮ በአለም ጤና ድርጅት (WHO) ውስጥ እያገለገሉ የሚገኙት ዶ/ር ቴድሮስ የህወሀት ቡድን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ሲያገለግሉ እንደነበር ይታወቃል፡፡

እንደ አውሮፓውያኑ ከ 2005 እስከ 2012 የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር እንዲሁም ከ 2012 እስከ 2016 ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነበሩ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም  and  Source – https://www.aa.com.tr/en/africa/ethiopia-who-director-general-works-as-tplf-diplomat/2046193