November 19, 2020

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክር ቤት በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አካሂዷል።

በምክክር መድረኩ ላይ በጊዜያዊ አስተዳደሩ መሪነት በክልሉ ሰላም ለማምጣት በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ምን መሆን አለበት የሚል ሐሳብ ተነሥቷል።–በክልሉ ሊሠሩ የታሰቡ ዐበይት ሥራዎች የተገለጹ ሲሆን፣ ባለ ስድስት ነጥብ ረቂቅ ቻርተር ዝግጅት መደረጉ ታውቋል።

ፓርቲዎቹ በአሁኑ ወቅት በክልሉ እየተካሄደ ላለው ሕግ የማስከበር ዘመቻ ግብ እስኪመታ ከመንግሥት እና ከመከላከያ ኃይል ጎን እንዲቆሙ ተጠይቋል። EBC