============

እኛ ተጋሩ ነን! እኛ ኢትዮጵያዊ አይደለንም! መሪ መፈክር ሆኖ ውሏል።

እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል —Adios!

እንዲህ ላስቀምጠው፡ – ኢትዮጵያዊነት ሲግል በጭልፋ፤ ሲበርድ በእፍኝ የሚዛቅ ማንነት አይደለም! ኢትዮጵያዊነት በተከታታይ ትውልዶች በደም ፍሳሽ፤ በአጥንት ክስካሽ የተገነባ ለሽሆች አመታት በተጋድሎ ተጠብቆ፤ ታፍሮ እና ተከብሮ የኖረ ማንነት እንጅ ከሀዲያን ሲፈልጉ እና እነሱ ስልጣን ሲኖራቸው ብቻ የሚወስዱት፣ ስልጣን ሲርቃቸው የሚከዱት እና የሚጠየፉት ማንነት አይደለም።

በበኩሌ የፖለቲካ ለበጡን ወደጎን አድርጌ ተጋሩወች ዛሬ ኖቨምበር 21/2020 በዋሽንግተን ዲሲ ተሰልፈው መፈክር እንዳሰሙት እምነቱ እና ምኞቱ ከሆነ Adios ከማለት ውጭ ምን ሊሆን ይቻላል? ከዚህ የተጋሩ ተብየወች ሰልፍ የሰማሁት የሕዝቡ ድምጽ ከሆነ ያለፉት 27 የጭቆና እና የሞት አመታት ለሌላው ኢትዮጵያዊ የቅኝ ግዛት ዘመን ነበር ማለት ነው። በእርግጥ ነው እጅግ ብዙ ሰማዕትነትን የከፈሉ የትግራይ ተወላጆች እና አርበኞች እንዳሉ እና እንደነበሩ ግልጽ ነው። ይህ የዋሽንግተን ሰላማዊ ሰልፍ ግን የክህደት መፈክር ሲያሰማ የካደው ቀሪውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ድርብርብ ክህደት የፈጠረው ለትግራይ ሰማዕታት ነው።

ህወሓትን ፊት ለፊት ገጥመው የወደቁት እነ ጓድ ጋይም፣ ኃይሌ አባይ እና እጅግ ብዙ ታጋይ መስዋእት ከፋዮች ነበሩ የእነዚያ ደም የፈሰሰውም በነዚህ የህወሓት ነፍሰበሎች እንደሆነ ግልጽ ነው። እናም የዲሲ ተጋሩ ነን ባይ ከሀዲያን “የትግራይን ኢትዮጵያዊነት” ሊነጥቁም ሆነ ሊደልዙ መብታቸው አይደለም። ትግራይ ከቀሪው የኢትዮጵያ አካልነት በተጋድሎ ትጠበቃለች። የባንዳ ልጆች ለአንዴም ለመጨረሻ ተቸንፈዋል!!

ዳግም ሊያንሰራሩም ሆነ ከገቡበት ማጥ ሊወጡ ፈጽሞ የማይታሰብ ነው። መደምደሚያው ወደታሪክ የቆሻሻ ጋርቤጅ ይጨመራሉ። ህወሓት ኢትዮጵያ ሆናም አታውቅ። ህወሓት መሰረታዊ የኢትዮጵያ ጠላት ናት የትግራይ ሕዝብን በቅኝ እና በኃይል እንጅ በውድ እና በፈቃድ ስለአልያዘች የተጀመረው ጸረ ህወሓት ትግል ቀጥሎ የማጥፋት ዘመቻው በህወሓት መቃብር ይደመደማል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!