ማሕበራችን በኢትዮጲያ አየር መንገድ ውስጥ እየተዘረጋ ያለውን የብሄርና የሃይማኖት የጎጥ ሰንሰለትን አጥብቆ ይቃወማል።
–
ማሕበራችን የኢትዮጲያ አየር መንገድ ግሩኘ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር ከተመሰረተበት ግዜ አንስቶ በበላይ አስዳደሩ የተለያዩ ጥቃቶች ሲደርሱበት ቆይቷል።
–

አምባገነኑ የአየር መንገዱ የበላይ አስተዳደር የማህበሩን መሪዎች እና ሌሎች ሰራተኞችን ማባረሩን እና ከሀገር ማሰደዱን ተያይዞታል።ይሕ በእንዲህ እንዳለ በበላይ አስተዳደሩ የሚደገፈው በድርጅቱ ውስጥ ያለው ሌላ ማህበር ለህገ-ወጡ አስተዳደር ሽፋን እየሰጠ እንደሆነ በመረጃ አረጋግጠናል።
–
ከዚህም አልፎ ይሕ ማሕበር ስር የሰደደ የዘር ጥላቻ እና አደገኛ የሆነ የፖለቲካ አጀንዳ ባላቸው ግለሰቦች መመራቱ እና ማሕበሩ በበላይ አስተዳደሩ መደገፉ ሁኔታውን አሳሳቢ አድርጎታል። የበላይ አስተዳደሩ የብሄርና የሃይማኖት ክፍፍልን ስራየ ብሎ እየፈጠረ መሆኑ ጠቋሚ ማሳያዎች መኖራቸው እንዳለ ሆኖ ፤ የማህበራችን አመራሮች ላይ መሰረተ-ቢስ የሆኑ ተመሳሳይ የቦሔር ተኮር ፖለቲካ ክሶችን ሲያሰማም ኖሯል::
–
የኢትዮጵያውናን ኩራት የሆነው የኢትዮጲያ አየር መንገድ በትውልድ ቅብብሎሽ ዛሬ ላይ የደረሰ ግዙፍ ኢትዮጲያዊ ድርጅት ቢሆንም ፤ እየታየ ያለው አደገኛ ብሔርና ሃይማኖት ተኮር እንቅስቃሴ ከአሁኑ ተወግዞ ካልተወገደ አየር መንገዳችንን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ሊወስደው ይችላል ብለን እናምናለን!
–
የአየር መንገዱን ሰራተኞች በብሔር እና በሀይማኖት በመክፈል ፤ ሀገሪቱን እየረበሸ ያለውን የእርስ በእርስ ጥላቻ አየር መንገድ ውስጥ ዘርቶ አየር መንገዳችንን የብሔርና የሃይማኖት አጀንዳ ማራመጃ ለማድረግ እየተደረገ ያለውን ጥረት ማምከን ይቻል ዘንድ ይህንን በበላይ አስተዳደሩ “ዝም” የተባለውን አጀንዳ ሁሉም ኢትዮጲያዊ ሊያወግዘው ይገባል!

Ethiopian Airlines Group Basic Trade Union
ማሕበራችን በ ኢትዮጲያ አየር መንገድ( Ethiopian Airlines) ውስጥ እየተዘረጋ ያለውን የብሄርና የሃይማኖት የጎጥ ሰንሰለትን አጥብቆ ይቃወማል።
ማሕበራችን የኢትዮጲያ አየር መንገድ ግሩኘ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር ከተመሰረተበት ግዜ አንስቶ በበላይ አስዳደሩ የተለያዩ ጥቃቶች ሲደርሱበት ቆይቷል።
አምባገነኑ የአየር መንገዱ የበላይ አስተዳደር የማህበሩን መሪዎች እና ሌሎች ሰራተኞችን ማባረሩን እና ከሀገር ማሰደዱን ተያይዞታል። … See More