24/11/2020

ኢሰመኮ መግለጫ

ትግራይ፡ የማይካድራ ሲቪል ሰዎች ጭፍጨፋ የግፍና ጭካኔ ወንጀል ነው!

የተጎዱትን ማቋቋም እና የአጥፊዎችን ተጠያቂነት ማረጋገጥ ይገባል፡፡

በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን በምትገኘው የማይካድራ ከተማ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በወቅቱ በስልጣን ላይ በነበረው የአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅርና ሳምሪ በተባለ ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን የተፈጸመው ጥቃት፤ ግድያ፣ ጉዳትና ውድመት፤ ጠቅላላ ድርጊቱና ውጤቱ ግፍና ጭካኔ የተሞላበት በሲቪል ሰዎች ላይ  የተፈጸመ የጭፍጨፋ ወንጀል (atrocious crime of massacre against civilians) መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ፡፡

ይህ የተገለጸው ኮሚሽኑ ከሕዳር 5 እስከ ሕዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ በማይካድራ ከተማ እንዲሁም በአብርሀጅራ፣ በሳንጃ፣ በዳንሻ፣ በሁመራ እና በጐንደር ከተማ ተዘዋውሮ ባደረገው ምርመራ የደረሰበትን ግኝቶች ይፋ ባደረገበት የመጀመሪያ ደረጃ ቀዳሚ ሪፖርት ነው፡፡ ይህ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል (crimes against humanity) እና የጦር ወንጀል (war crime)  ሊሆን እንደሚችል የሚያመለክት ስለሆነ ኮሚሽኑ ዝርዝር ማስረጃዎቹን እና ወንጀሉን የሚያቋቁሙትን የሕግና የፍሬ ነገር ትንተና በሙሉ ሪፖርቱ ላይ በዝርዝር አጣርቶ የሚያቀርብ መሆኑን አሳውቋል፡፡

በቀዳሚ ሪፖርቱ እንደተመለከተው በአካባቢው የነበረው የሚሊሽያና የፖሊስ ጸጥታ መዋቅር በፌዴራሉ አገር መከላከያ ሰራዊት እርምጃ ሸሽቶ አካባቢውን ለቅቆ ከመውጣቱ በፊት ሳምሪ ከተባለ መደበኛ ያልሆነ የትግራይ ወጣቶች ቡድን ጋር በማበርና በመተባበር በተለይ ‹‹አማሮችና ወልቃይቴዎች›› ያሏቸውን የአካባቢው ነዋሪ ሲቪል ሰዎች ከቤት ቤት እየዞሩና በየጐዳናው ላይ በገመድ በማነቅ፣ በስለት በመጥረቢያ በዱላ በመደብደብ ገድለዋል፣ የአካል ጉዳት አድርሰዋል፣ እንዲሁም ንብረት አውድመዋል፡፡ ኢሰመኮ ከአካባቢው ምንጮች እስከ አሁን በአገኘው መረጃ በአነስተኛ ግምት እስከ 600 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ትክክለኛው ቁጥር ከዚህ ሊበልጥም እንደሚችል በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡

ሳምሪ የሚባለው የትግራይ ወጣቶች ቡድን በዚህ ከባድ ወንጀል ላይ ቢሰማራም፤ በአንጻሩ የትግራይ ብሔረሰብ ተወላጅች የሆኑ ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች አጥቂው ቡድን ሲያሳድዳቸው የነበሩ ሲቪል ሰዎችን በቤታቸው፣ በቤተክርስቲያን እና በእርሻ ቦታ ደብቀው በመሸሸግ ሕይወታቸውን እንዳተረፉላቸው ኢሰመኮ ያነጋገራቸው ምስክሮች አረጋግጠዋል፡፡

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ‹‹በማይካድራ ከተማ በአነስተኛ ጽንፈኛ ቡድን የተፈጸመው በብሔር ማንነት ላይ የተመሰረተ እጅግ ዘግናኝ ኢሰብዓዊ ወንጀል ልብ ሰባሪ ቢሆንም፤ በአንጻሩ ኢትዮጵያውያን በብሔር ሳይለያዩ አንዱ የሌላው ጠባቂ ሆነው መታየታቸው ልብ ይጠግናል፤ ስለ ወደፊት በሰላም አብሮ መኖርም ተስፋ ይሰጣል›› ብለዋል፡፡ አክለውም ‹‹የተጐዱ ሰዎችን እና አካባቢዎችን መልሶ ከማቋቋምና ከመጠገን በተጨማሪ፤ በዚህ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ወንጀል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የተሳተፉ በየደረጃው ያሉ ጥፋተኞችን በሕግ ፊት ተጠያቂነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል›› ብለዋል፡፡

የኮሚሽኑን የመጀመሪያ ደረጃ ቀዳሚ ሪፖርት ከዚህ ጋር ተያይዟል፡፡ https://docs.google.com/document/d/1GjeMuFv0nvqX4tMGWc0vZ2jDm0uryGWHobrrN5GW3HM/edit?usp=sharing

የማይካድራው ጭፍጨፋ በሕወሓት የፀጥታ መዋቅር የተፈፀመ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን ይፋ አድርጓል።

November 24, 2020

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን የማይካድራው ጭፍጨፋ በትህነግ የፀጥታ መዋቅር የተፈፀመ መሆኑን ይፋ አድርጓል። በጭፍጨፋው በትንሹ 600 ያህል ንፁሃን ተገድለዋል ብሏል። የሟቾች ቁጥር ከዚህም ከፍ ሊል ይችላል ብሏል።

ኢሰመኮ መግለጫ

ኅዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም.

ትግራይ፡ የማይካድራ ሲቪል ሰዎች ጭፍጨፋ የግፍና ጭካኔ ወንጀል ነውየተጎዱትን ማቋቋም እና የአጥፊዎችን ተጠያቂነት ማረጋገጥ ይገባል

በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን በምትገኘው የማይካድራ ከተማ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በወቅቱ በስልጣን ላይ በነበረው የአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅርና ሳምሪ በተባለ ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን የተፈጸመው ጥቃት፤ ግድያ፣ ጉዳትና ውድመት፤ ጠቅላላ ድርጊቱና ውጤቱ ገለጸ፡፡

ግፍና ጭካኔ የተሞላበት በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመ የጭፍጨፋ ወንጀል (atrocious crime of massacre against civilians) መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)

ይህ የተገለጸው ኮሚሽኑ ከሕዳር 5 እስከ ሕዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ በማይካድራ ከተማ እንዲሁም በአብርሀጅራ፣ በሳንጃ፣ በዳንሻ፣ በሁመራ እና በጐንደር ከተማ ተዘዋውሮ ባደረገው ምርመራ የደረሰበትን ግኝቶች ይፋ ባደረገበት የመጀመሪያ ደረጃ ቀዳሚ ሪፖርት ነው፡፡ ይህ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል (crimes against humanity) እና የጦር ወንጀል (war crime) ሊሆን እንደሚችል የሚያመለክት ስለሆነ ኮሚሽኑ ዝርዝር ማስረጃዎቹን እና ወንጀሉን የሚያቋቁሙትን የሕግና የፍሬ ነገር ትንተና በሙሉ ሪፖርቱ ላይ በዝርዝር አጣርቶ የሚያቀርብ መሆኑን አሳውቋል፡፡

በቀዳሚ ሪፖርቱ እንደተመለከተው በአካባቢው የነበረው የሚሊሽያና የፖሊስ ጸጥታ መዋቅር በፌዴራሉ አገር መከላከያ ሰራዊት እርምጃ ሸሽቶ አካባቢውን ለቅቆ ከመውጣቱ በፊት ሳምሪ ከተባለ መደበኛ ያልሆነ የትግራይ ወጣቶች ቡድን ጋር በማበርና በመተባበር በተለይ ‹‹አማሮችና ወልቃይቴዎች›› ያሏቸውን የአካባቢው ነዋሪ ሲቪል ሰዎች ከቤት ቤት እየዞሩና በየጐዳናው ላይ በገመድ በማነቅ፣ በስለት በመጥረቢያ በዱላ በመደብደብ ገድለዋል፣ የአካል ጉዳት አድርሰዋል፣ እንዲሁም ንብረት አውድመዋል፡፡ ኢሰመኮ ከአካባቢው ምንጮች እስከ አሁን በአገኘው መረጃ በአነስተኛ ግምት እስከ 600 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ትክክለኛው ቁጥር ከዚህ ሊበልጥም እንደሚችል በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡

ሳምሪ የሚባለው የትግራይ ወጣቶች ቡድን በዚህ ከባድ ወንጀል ላይ ቢሰማራም፤ በአንጻሩ የትግራይ ብሔረሰብ ተወላጅች የሆኑ ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች አጥቂው ቡድን ሲያሳድዳቸው የነበሩ ሲቪል ሰዎችን በቤታቸው፣ በቤተክርስቲያን እና በእርሻ ቦታ ደብቀው በመሸሸግ ሕይወታቸውን እንዳተረፉላቸው ኢሰመኮ ያነጋገራቸው ምስክሮች አረጋግጠዋል፡፡

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ‹‹በማይካድራ ከተማ በአነስተኛ ጽንፈኛ ቡድን የተፈጸመው በብሔር ማንነት ላይ የተመሰረተ እጅግ ዘግናኝ ኢሰብዓዊ ወንጀል ልብ ሰባሪ ቢሆንም፤ በአንጻሩ ኢትዮጵያውያን በብሔር ሳይለያዩ አንዱ የሌላው ጠባቂ ሆነው መታየታቸው ልብ ይጠግናል፤ ስለ ወደፊት በሰላም አብሮ መኖርም ተስፋ ይሰጣል›› ብለዋል፡፡ አክለውም ‹‹የተጐዱ ሰዎችን እና አካባቢዎችን መልሶ ከማቋቋምና ከመጠገን በተጨማሪ፤ በዚህ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ወንጀል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የተሳተፉ በየደረጃው ያሉ ጥፋተኞችን በሕግ ፊት ተጠያቂነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል›› ብለዋል፡፡

የኮሚሽኑን የመጀመሪያ ደረጃ ቀዳሚ ሪፖርት

ትግራይ ፡ በማይካድራ ከ600 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ – ቢቢሲ / አማርኛ

ከ 8 ሰአት በፊት

ጥቃቱ ተፈጸመ የተባለበት ማይካድራ ከሁመራ ከተማ በቅርብ እርቀት ላይ ትገኛለች
የምስሉ መግለጫ, ጥቃቱ ተፈጸመ የተባለበት ማይካድራ ከሁመራ ከተማ በቅርብ እርቀት ላይ ትገኛለች

በማይካድራ ከተማ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ቢያንስ 600 ሰዎች መገደላቸውንና ቁጥሩም ከዚህ እንደሚበልጥ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ።

ኮሚሽኑ ይህንን የገለጸው በማይካድራ ከተማ የተከሰተውን ጥቃት ተከትሎ በከተማዋና በአካባቢው ባሉ ሌሎች ስፍራዎች ያካሄደውን ምርመራ ይፋ ባደረገበት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ላይ ነው።

ከሁለት ሳምንት በፊት በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ክፍል በምትገኘው የማይካድራ ከተማ የተፈጸመው ጥቃት በአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅርና ‘ሳምሪ’ በተባለ ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን መፈጸሙንም ኢሰመኮ በሪፖርቱ ላይ አመልክቷል።

በዚህም መሰረት የአካባቢው መስተዳድርና ‘ሳምሪ’ በተባለው ቡድን የተፈጸመው ጥቃት፤ ግድያ፣ ጉዳትና ውድመት፤ ጠቅላላ ድርጊቱና ውጤቱ “ግፍና ጭካኔ የተሞላበት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመ የጭፍጨፋ ወንጀል” ነው ሲል ኮሚሽኑ ገልጾታል።

ኮሚሽኑ ይህ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት “በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል እና የጦር ወንጀል ሊሆን እንደሚችል” ያመለከተ ሲሆን፤ ለዚህም ኢሰመኮ ዝርዝር ማስረጃዎቹን እና ወንጀሉን የሚያቋቁሙትን የሕግና የፍሬ ነገር ትንተና በሙሉ ሪፖርቱ ላይ በዝርዝር አጣርቶ የሚያቀርብ መሆኑን አሳውቋል።

ይህ ድርጊት በማይካድራ የነበረው የሚሊሽያና የፖሊስ መዋቅር የፌዴራሉ ሠራዊትን እርምጃ ሸሽቶ አካባቢውን ለቆ ከመውጣቱ በፊት “ሳምሪ ከተባለ መደበኛ ያልሆነ የትግራይ ወጣቶች ቡድን ጋር በመተባበር በተለይ “አማሮችና ወልቃይቴዎች” ያሏቸው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት” መፈጸማቸውን አመልክቷል።

በዚህም ቡድኑ “ከቤት ቤት እየዞሩና በየጐዳናው ላይ ያገኙትን ሰው በገመድ በማነቅ፣ በስለት፣ በመጥረቢያ፣ በዱላ በመደብደብ ገድለዋል፣ የአካል ጉዳት አድርሰዋል፣ እንዲሁም ንብረት አውድመዋል” ሲል ኮሚሽኑ ገልጿል።

ኮሚሽኑ ጨምሮም “‘ሳምሪ’ የሚባለው የትግራይ ወጣቶች ቡድን በዚህ ከባድ ወንጀል ላይ ቢሰማራም፤ በአንጻሩ የትግራይ ብሔረሰብ ተወላጆች የሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች አጥቂው ቡድን ሲያሳድዳቸው የነበሩ ሰዎችን በቤታቸው፣ በቤተክርስቲያንና በእርሻ ቦታ ደብቀው እንዳተረፏቸው” ኢሰመኮ ምስክሮችን ጠቅሶ በሪፖርቱ ላይ አስፍሯል።

በተጨማሪም የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) “በማይካድራ በአነስተኛ ጽንፈኛ ቡድን የተፈጸመው በማንነት ላይ የተመሰረተ እጅግ ዘግናኝ ወንጀል ልብ ሰባሪ ቢሆንም፤ በአንጻሩ ኢትዮጵያውያን በብሔር ሳይለያዩ አንዱ የሌላው ጠባቂ ሆነው መታየታቸው ልብ ይጠግናል” በማለት ለወደፊቱ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ ጨምረውም በዚህ ጥቃት የተጎዱ ሰዎችንና አካባቢዎችን መልሶ ከማቋቋምና በተጨማሪ፤ “በዚህ ከባድ ወንጀል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የተሳተፉ በየደረጃው ያሉ ጥፋተኞችን በሕግ ፊት ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም በማይካድራ ከተማ የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ያደረገውን ምርመራ በተመለከተ ያወጣው ባለስድስት ገጽ ዘገባ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት እንደሆነ አመልክቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጥቃቱን የፈፀሙት የህወሓት ታጣቂዎች ናቸው ቢሉም የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በበኩላቸው በግድያዎቹ እጃችን የለበትም በማለት ውድቅ አድርገውታል።

የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ውንጀላው “መሰረት” የሌላው ነው በማለት፤ ጥቃቱ በገለልተኛ ወገን ይጣራ ማለታቸው የሚታወስ ነው።

ከሳምንት በፊት ስለክስተቱ ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ አምነስቲ ኢንትርናሽናል በማይካድራ ስለተፈጸመው ጥቃት ተመሳሳይ ሪፖርት ማውጣቱ ይታወሳል።

ክስተቱን ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኃላፊ ሚሼል ባችሌት በማይካድራ ከተማ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል የሚለው ሪፖርት እንዲጣራ መጠየቃቸው የተዘገበ ሲሆን በተጨማሪም “ግድያዎቹ መረጋገጥ ከቻሉ እንደ ጦር ወንጀል ይቆጠራል” በማለት ድርጅቱ ማስጠንቀቁ ይታወሳል።

በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊትና የትግራይ ክልል ኃይሎች ወታደራዊ ግጭት ውስጥ ከገቡ ከሳምንት በኋላ በምዕራብ ትግራይ የተካሄደውን ግጭት ተከትሎ ነበር በማይካድራ ከተማ ውስጥ ሰላማዊ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የሚያመልክቱ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ፎቶግራፎች መታየት የጀመሩት።

አምነስቲ ኢንትርናሽናልም የእነዚህን ምስሎች እውነተኝነት በማረጋገጥና የዓይን እማኞችን በማነጋገር በከተማዋ ውስጥ ማንነትን መሰረት ያደረገ አሰቃቂ ጥቃት መፈጸሙን ከሳምንት በፊት ባወጣው መግለጫ ማሳወቁ ይታወሳል።

በእንግሊዝኛ ቋንቋ

EHRC Press Statement

24 November 2020

TIGRAY: MAIKADRA MASSACRE OF CIVILIANS IS A CRIME OF ATROCITYREHABILITATE VICTIMS AND BRING PERPETRATORS TO JUSTICE

The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) has found that an atrocious massacre of civilians has been committed by an informal group of Tigrayan youth known as ‘Samri’, aided and abetted by members of what was then the local administration and security establishment in Maikadra, in Tigray Region’s Western Zone, on November 9th, 2020.

EHRC visited Maikadra, Abrhajira, Sanja, Dansha, Humera, and Gonder between November 14 – 19, 2020, as part of its investigation into human rights violations, preliminary findings of which were released today.

The preliminary findings state that what transpired in Maikadra on November 9th, 2020, including the killings, bodily and mental injury, as well as the destruction that went on throughout the night, the overall conduct and results thereof, strongly indicate the commission of grave human rights violations which may amount to crimes against humanity and war crimes. The full extent of the evidence and elements of the crime will be further examined in detail in the full report.

The preliminary report finds that before retreating from the advance of the Ethiopian National Defense Forces (ENDF), the local militia and police security apparatus joined forces with members of the Samri group to carry out door-to-door raids and kill hundreds of people they identified as ethnic “Amharas and Wolkait origin”, by beating them with sticks, stabbing them with knives, machetes and hatchets and strangling them with ropes. They also severely injured many people and looted or destroyed properties. Based on testimony gathered so far, EHRC estimates that at least 600 civilians were killed. The death toll could be higher still as there are reports of individuals unaccounted for at the time of EHRC’s visit and bodies hidden in fields outside Maikadra.

Amidst the harrowing acts of the Tigrayan informal youth group, Samri, survivors also tell many stories of humane actions where other residents also of ethnic Tigrayan origin, who saved many lives by hiding targets in their homes, in churches and in farms fields.

EHRC’s Chief Commissioner Daniel Bekele said, “The unimaginably atrocious crime committed against civilians for no reason other than their ethnicity is heartbreaking. Yet we are consoled by the stories of Ethiopians who saw beyond ethnic origin to come to the aid of their compatriots in their time of need. These stories keep the hope of a return to peaceful coexistence going”.

“It is now an urgent priority that victims are provided redress and rehabilitation, and that perpetrators involved directly or indirectly at all levels are held to account before the law.”