November 25, 2020Konjit Sitotaw

ሱዳን ላይ የተቋቋመውን የስደተኞች መጠለያ ካምፕ የጎበኙት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ኦፊሰር ትዝብታቸውን ሲያካፍሉ ከዚህ በፊት ግጭት በሚከሰትባቸው ቦታወች በሚከሰቱ ስደቶች ለየት ባለ መልኩ ከኢትዮጲያ የትግራይ ክልል ወደ ካምፑ እየገቡ ያሉት ስደተኞች አብዛኛወቹ ወንድ ወጣቶች መሆናቸው አስገራሚ ነው ብለዋል። ኦፊሰሩ እንደሚሉት ብዙውን ጊዜ ግጭቶች ሲፈጠሩ የሚሰደዱት በአብዛኛው ሴቶች፣ ህጻናት እና አቅመ ደካማወች ሲሆኑ አሁን እየታየ ያለው ግን ወንዶች ናቸው ብለዋል።

ቪዲዮውን ከ22.50 ጀምሮ ያዳምጡት

Press conference by Babacar Cissé, UN Resident Coordinator and Humanitarian Coordinator for Sudan, who led a mission to the border area with Ethiopia. Mr. Cissé.

http://webtv.un.org/search/the-situation-in-ethiopia-press-conference-19-november-2020/6211020983001/?term=Ethiopia&sort=date&fbclid=IwAR1CJ0zw7h6PrS3WeDp7CwTUtZBLoFRkXcD_nn_tMFy5Z0ljYIY4ZXU-Vbc

ከሁመራ ወደ ሱዳን የተሰደዱት በምግባር ሲተነተኑ እነማን ናቸዉ?

1) ጦርነቱን መቋቋም ያቃተዉ የትህነግ ልዩ ሃይልና ይሄ ሀይል ሱዳን ሄዶ ራሱን አደራጅቶ እንደገና አማራን ለማጥቃት ያሰበዉ ሀይል ነው።

2) የሀገር አለኝታ የሆነዉን መከላከያን በተኛበት ከትህነግ ጋር ተመሳጥሮ አብሮ መክሮ በጭፍጨፋዉ የተሳተፈዉ የትግራይ ሚሊሻ አባላት፣

3) በትህነግ ጥሪ መሰረት ዜጎችን ጨክኖ ሲያርድ የነበረዉ ሳምሪ የተባለዉ ገዳይና አስገዳይ ቡድን አባላት።

4) አማራንና ኢትዮጵያን ለማጥፋት አልሞ ሲሰራ የነበረዉ የትግራይ የአመራር መዋቅር በሙሉ

5) ህወሓትን በገንዘብና በማቴሪያል የሚደግፈዉ ባለሀብት በሙሉ፣

6) አገር እንድትፈርስ፣ አማራ እንዲጠፋ፣ የአገራችን መንግስት አጣብቂኝ ዉስጥ እንዲገባና ህዝብ ከህዝብ ጋር እንዲጫረስ ሲሰራ የነበረዉ የትግራይ ኤሊት(አክቲቪስት) የደህንነትና የመረጃ ሀይል፣

7) ንፁህ ዜጎች፣ እናቶች ሴቶችና ህፃናት እንዲሁም በእድሜ የገፉ አዛዉንቶች።

ከኢትዮጲያ የትግራይ ክልል ወደ ካምፑ እየገቡ ያሉት ስደተኞች አብዛኛወቹ ወንድ ወጣቶች መሆናቸው አስገራሚ ነው – የስደተኞች ኮሚሽን ኦፊሰር