በቡለን፣ በድባጤ፣ ማንዱራ እና ዳንጉር ወረዳዎች ዛሬም ተጨማሪ የሰው ሕይወት ማለፉን የመተከል ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡የክልሉ መንግስት ወንጀል ፈፃሚዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ አለመሆኑንም ተናግረዋል፡፡
–
(አብመድ) በመተከል ዞን አርቆ የማሰብ የሞራል ልዕልና በሌላቸው አንዳንድ አመራሮችና የጥፋት ኃይሎች ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን ከሰሞኑ አብመድ መዘገቡ ይታወሳል፡፡
–

በቡለን፣ በድባጤ፣ ማንዱራ እና ዳንጉር ወረዳዎች ዛሬም ተጨማሪ የሰው ሕይወት ማለፉን በመተከል ዞን ተፈናቃይ አርሶአደሮች ተናግረዋል፡፡ በአካባቢው ወንጀል ፈጻሚዎች ላይ አሁንም ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ አይደለም ብለዋል፡፡
–
ሲፈናቀሉ ትተዋቸው የመጡት የቀንድ ቀብቶች ሙሉ በሙሉ እንደተወሰዱባቸውም አርሶአደሮቹ ተናግረዋል፡፡
–
ወቅቱ ዓመቱን ሙሉ የለፋንበትን ሰብል የምንሰበስብበት ጊዜ በመሆኑ ሰላም ተፈጥሮ ወደ ቀያችን በመመለስ የደረሱ ሰብሎችን መሰብሰብ የምንችልበት ሁኔታ ይፈጠርልን ሲሉም ተፈናቃይ አርሶአደሮች ጠይቀዋል፡፡
–
ግድያውም ከፓዌ ወረዳ በስተቀር በሁሉም ወረዳዎች ዛሬም እየደረሰ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም እና ህዝብ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ ጋሹ ዱጋዝም አምነዋል፡፡–አቶ ጋሹ ዱጋዝ በመተከል ዞን በሚገኙ ስድስቱም ወረዳዎች አስተማማኝ ሰላም እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እየተሰራ እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡
–
ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እስኪመለሱ ድረስ ደግሞ የፀጥታው ኃይል ከጎናቸው ሆኖ የደረሱ ሰብሎችን እንዲሰበሰቡ ይደረጋል ነው ያሉት፡፡