26/11/2020

..(ዶክተር ዳንኤል በቀለ ለፋና ከሰጡት ቃለ-ምልልስ የተወሰደ ነው).ትሕነግ በማይካድራ ማንነትን መሠረት አድርጎ ከ600 በላይ ንፁሓንን ጨፍጭፏል

 * የማይካድራውፍጅት የመርሃ-ግብሩ ቅደም ተከተልና ቅድመ ዝግጅት   .

* ጭፍጨፋው ……., ዝግጅት ተደርጎበታል ። * ጥቃቱ ተግባራዊ የሆነው በታጣቂዎች ጥበቃና ከለላ እየተደረገለት ይንቀሳቀስ ከነበረው  ” ሳምሪ ” እየተባለ የሚጠራው የአካባቢው የወጣቶች አደረጃጀት ነው ።

* ወጣቶቹ …. በአካባቢውም የሚታወቁ ናቸው ።

* ጥቃቱንም ሲፈፅሙ በሚሊሻና በፖሊስ እየታጀቡና ከቤት ቤት እየዞሩ ነው ።

* ጭፍጨፋውና ግድያው በዱላ ፣ በስለት ፣ በጩቤ ፣ በፋስ ፣ በመጥረቢያ ግማሾቹ ደግሞ በገመድ አንገታቸው እየታነቀ ነው ።

* ቡድኑ በተለይም የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ትኩረት አድርጎ ነው ጭፍጨፋውን ያከናወነው ።

* ቀደም ሲል ሰዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ መመሪያ ተላልፎላቸውል ።

* ገዳይ ወጣቶቹ በከተማው መውጫና መግቢያ ቦታዎች ከአካባቢው ሚሊሻና ፖሊስ ጋ በመቀናጀት ኬላ አቋቁመው ሰው እንዳይገባና እንዳይወጣ ሲቆጣጠሩ የነበር ።

* ሰዎች ማንነታቸውን ለመለየት በመታወቂያቸው ጭምር የመለየት ስራ ተከናውኗል ።

* የሱዳን ሲም ካርድ ያላቸው ሰዎች ስም ካርዳቸው ተወስዶ እንዲሰባበር ተደርጓል ፣ * ከዚህ በሗላ ጥቅምት 30 መንገድ የመዝጋቱ ሒደት በከፍተኛ ደረጃ ተጠናቀቀ ።

* በተጠቀሰው ቀን 5 ሰአት ላይ ተጨማሪ የማንነት ማጣራት ተግባር ተከናወነ ።

* ከሰአት በሗላ 9 ሰአት ላይ የመጀመሪያው ጥቃት ተፈፀመ ።

* ቀጥሎ ለሊቱን ሙሉ ሲካሄድ አነጋ ። * ሊያመልጡ የሞከሩ በጥይት ተመተው ተገለዋል ።

* በጥቃቱ ሊስት ውስጥ የሌሉ ግን ደግሞ ተጠቂዎችን ለማዳን የሞከሩ  የግድያው ሰለባ ሆነዋል ።

* ጠዋት ጥቃቱን ሲፈፅሙ ያነጉት ቡድኖች (ሳምሪዎች )  ፣ ሚሊሻዎችና ፖሊሶች ከተማውን ለቀው ወጥተዋል ።