November 29, 2020 – Mereja.com
“ዐማራዬ ስማኝማ !!” በሚል ርዕስ ከመምህር ዘመድኩን ለዐማራ ህዝብ የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት
… እርግጥ ነው ዝንተዓለሙን በላይህ ላይ ተጠምጥሞ ደምህን እየመጠጠ፣ ሥጋህን እየቀረጠፈ፣ አጥንትህን እየጋጠ፣ አላስተነፍስ፣ አላላውስ፣ አላንቀሳቅስ፣ አላስበላ፣ አላስጠጣ፣ አላስተኛ ብሎ ሰቅዞ የያዘህን የሰሜኑን ዘንዶ አናት አናቱን ፈጥርቀህ ተገላግለኸዋል። ይሄ ታዲያ ለጊዜው ነው።
… ዘንዶው ግን ብቻውን እንዳልሆነ እወቅ። ዘንዶው ልጆች አሉት። ቀሩጥ እሱን ፍሬዎችም አሉት። ዘርም አለው። ኦነግ የሚባል የበኩር ልጅ አለው። ኦነግ የበኩር ልጁ ነው። ኢህአዴግ የሚባሉ የመዋጮ የጉዲፈቻ ልጆችም አሉት። በረሃ ላይ በቀትር ፀሐይ የሰንበት ጽንስ የሆኑ ልጆች አሉት። ብአዴን የሚባል የእንግዴ ልጅም ልጁ ነው። ኦህዴድም የኦነግ መንትያ የህወሓት ዲቃላ ነው። ደኢህዴን የሚባልም ዲዳ ዱዳም ልጅ አለው። ልጆቹ የተደራጁ ናቸው። አሁንም ከዚያው ከዙፋኑ ላይ ናቸው። ዘንዶው በማርጀቱ ናቁት፣ ጠሉት፣ እንዲወገድ አደረጉት እንጂ የዘንዶው ልጆች አሁንም በህይወት አሉ። የዘንዶ ልጅ ደግሞ ያው ዘንዶ ነው። የእባብ ልጅም እባብ ነው። ከእባብ እንቁላል የርግብ ጫጩት በፍፁም አይፈለፈልም። የጅብ ልጅ ጅብ ነው። የፈለገ ብታንቆለጳጵሰው፣ ብታሳምረው፣ ብታለብስ ብታሽሞነምነው። የጅብ ልጅ ያው ጅብ ነው። እናም ገና ከፍተኛ የቤት ሥራ ከዘንዶዎቹ ልጆች ይጠብቅሃልና ብዙም አትዘናጋ። ቆቅ ሁን ለማለት ነው።
… ጥይትህን በባዶ ሰማይ ላይ አትበትነው። አትጨርሰውም። አታባክነው። ደስታህን በልክ አድርገው። ሕገ አራዊት ተብዬው ሕገ መንግሥት ገና ከዙፋኑ መች ተነሣና፣ መች ተላቀቀና። ወዳጄ ከመቀሌ ዘመቻ መልስ ምን እንደተደገሰልህ አታውቅምና የሆነውን እስክትሰማ ድረስ ብዙም አትንቀዥቀዥ። ፈንጠዝያህን በልክ አድርገው። መቀሌ ተይዟል ማለት ወያኔ አብቅቶላታል ማለት አይደለም። ይሄን አትርሳ። የወያኔ ልጆች አሁንም መሪዎችህ ናቸው። የዘንዶው ልጆች አሁንም ገዢዎችህ ናቸው። ጠገዴን ፈርመው፣ መተከልን ቆርሰው፣ ደራን ጎምደው፣ ሸዋን ደርምሰው የሸጡብህ አሁንም ከሥልጣን ከአናትህ ላይ ናቸው። እናም ተረጋጋ አባው። ሁሉም በልክ ይሁን። ሰከን በል። ይልቅ ሥራህን ሥራ። በርህን፣ ደጃፍን አጠባብቀው። ቀዳዳህንም ድፈን።
… ህወሓት ሰፍታ የሰጠችህን ባንዴራ መች ከአናትህ ላይ አወረድክ? መች ከግቢህ ከደጃፍ ከአደባባይህ አስወገድክ? ህወሓት የሰፋችልህን ጥብቆ ገና መች አወለቅክ? ህወሓት የለጠፈችብህን ኮተት መች አራገፍክ? ባንዴራው እንዳለ እኮ ነው። ምኑም መቼ ተቀየረና፣ የገራፊ፣ የገዳይህን፣ የዘር አጥፊህን ባንዴራ አናትህ ላይ ተክለህ ህወሓት ሞተች፣ ጠፋች ብለህ ጥይትክን አትጨርስ። ነግሬሃለሁ ተረጋጋ። የፊልሙ ክፍል ሁለት መቼ ጀመረና ነው እንዲህ የምትሆነው። አትደሰት አላልኩም፣ ያለልክ አትጨፍር፣ አሁንም በጠሎትህ ትጋ፣ ገና ነው ገና ነው ነው የምልህ።
… በባህርዳር ያለውን የሰማእታት ሃውልት አይተኸዋል አይደል? ዐማራን ነፍጡን ዘቅዝቀን፣ አከርካሪውን አድቅቀን አንገቱን ሰብረን ቀብረነዋል ብለው ከደጃፍህ፣ ከሳሎንህ ላይ የተከሉልልህን አይተኸዋል አይደል? አርበኛው አባትህን፣ አረጋዊውን ነፍጠኛ፣ ሃገር አቅኚውን አባትህን እኮ ነው በገዛ ልጆቹ ፊት አንገቱን አስደፍተው አንተን በየአደባባዩ አናትህን በአግአዚ ስናይፐር እየቀነደሹ ሲደፉህ የኖሩት። አሁንም ያሉት። እናም ገና ብዙ የቤት ሥራ አለብህና ሙያ በልብ ብለህ ተረጋጋ። ደግሞም ዳኛው የሚለውንም ነቃ ብለህ ስማ።
… ሁለት ነገር ከዐማራ ምድር በተሎ አስወግድ። ከክፍለ ሃገሩም አውጣ። በጉልበት ሳይሆን በሕግ፣ በሥነ ሥርዓት ከላይህ ላይ ግፈፍ። አራግፍ፣ አስወግድም። ትግሬዎቹ የህወሓት ልጆች እንዳይስቁብህ በቶሎ ፈጽማቸው።
፩ኛ፦ ገዳይህ፣ አራጅህ፣ የዘርህ አጥፊህ፣ የዘር አምካኝህ፣ ዘራፊህ፣ አራጅህ፣ ደም አፍሳሿ፣ ርስትህን ነጣቂዋ፣ አላጋጯ፣ መርዘኛዋ፣ ታሪካዊ ጠላትህ፣ ሃይማኖት አልባዋ፣ ፀረ ኦርቶዶክስ፣ ፀረ ዐማራዋ፣ ነውረኛዋ፣ አውሬዋ፣ ደም መጣጯ፣ ዘራፊ ቀማኛ፣ ሌባ ወንበዴ፣ ማፍያዋ፣ ሽፍታዋ፣ ነቀርሳዋ፣ ዘማዊዋ፣ ዘንዶዋ፣ አጅሪት ህወሓት አሰፍታ የሰጠችህንና በክልልህ እየተውለበለበ እሷን እያስታወስክ እንድትኖር የሚያደርግህን ቀይ በቢጫ ደም በደም የኮሚኒስት ባንዴራዋን በአስቸኳይ አስወግድ። የገዳይህን ፎቶ በሳሎንህ አትስቀል።
፪ኛ፦ እነ አቦይ ስብሃት ነጋ እና እነ በረከት ስምዖን እነ አዲሱ ለገሰ እና እነ ታደሰ ጥንቅሹ እነ ተፈራ ዋልዋ በጋራ ሆነው በእምብርትህ ላይ አንገቱን ደፍተው፣ ነፍጡን ዘቅዝቀው የሠሩትን ሃውልት በሌላ፣ በፋኖው፣ በደመመራራው፣ በምሽግ ደርማሹ፣ በአነጣጥሮ ነጥሎ መቺው፣ በህወሓት አለቃው፣ በምትሃተኛው፣ መከላከያን፣ ኢትዮጵያንና ዐቢይ አሕመድን ራሱን በአዳነው፣ ከሞትም ባተረፈው በዐማራ ፋኖ ቀይረው። የዐማራ ልዩ ኃይል ጥይት በማይመታው በድግምት ነው የሚዋጋው ብለው በመሰከሩለት በረቂቁ የዐማራ ፋኖ ቀይረው። የዐማራን አረጋዊ ነፍጠኛ አባት ቀና አድርገህ ሃውልቱን አቁመው። ይሄን በተሎ ፈጽመው።
… ዐማራዬ ሰምተሃል!! አንተ ነፃ ውጣና እኔንም ለሃገሬ አብቃኝ። ወደ ሃገሬ መግቢያ መሻገሪያ የሰበሩብኝን ድልድይ ጠግነውና ለሃገሬ አብቃኝ። ብአዴንን ነፃ እንዳወጣህ፣ ትግሬንም ነፃ እንዳወጣህ፣ መከላከያንም ነፃ እንዳወጣህ፣ የዐቢይ አሕመድን መንግሥት ከሞት እንዳዳንከው እኔንም፣ ቤተሰቤንም፣ ኢትዮጵያ ሃገራችንንም ነፃ ታወጣን ዘንድ በጉጉት እየጠበቅኩህ ነው። መተከልም፣ ሙሉ ሸዋም፣ መላ ኢትዮጵያም እየጠበቅንህ ነው።
… ከኑመ ጋ ዱቢን!!
የወያኔ የሽንት ጨርቅ፣ ዳይፐር ቀይረው። ከዐማራ ምድር አስወግደው። የገዳይህን፣ የአራጅህን ስጦታ ከሳሎንህ አስወግደው። ኣ !
… ገዳይህ፣ አራጅህ፣ የዘርህ አጥፊህ፣ የዘር አምካኝህ፣ ዘራፊህ፣ አራጅህ፣ ደም አፍሳሿ፣ ርስትህን ነጣቂዋ፣ አላጋጯ፣ መርዘኛዋ፣ ታሪካዊ ጠላትህ፣ ሃይማኖት አልባዋ፣ ፀረ ኦርቶዶክስ፣ ፀረ ዐማራዋ፣ ነውረኛዋ፣ አውሬዋ፣ ደም መጣጯ፣ ዘራፊ ቀማኛ፣ ሌባ ወንበዴ፣ ማፍያዋ፣ ሽፍታዋ፣ ነቀርሳዋ፣ ዘማዊዋ፣ ዘንዶዋ፣ አጅሪት ህወሓት አሰፍታ የሰጠችህንና በክልልህ እየተውለበለበ እሷን እያስታወስክ እንድትኖር የሚያደርግህን ቀይ በቢጫ ደም በደም የኮሚኒስት ባንዴራዋን በአስቸኳይ አስወግድ። እደግመዋለሁ የገዳይህን ፎቶ በሳሎንህ አትስቀል።