
“የወልቃይት እና የራያ ህዝብ የተጨቆነው በህውሃት ብቻ አይደለም፤ እኛም ተጨምረን ነው ፍዳቸውን ያበዛነው” – (አቶ ገዱ አንዳርጋቸው)የአማራ ህዝብ የታገለው ርስት ለማስመለስ አይደለም። ይህንን Frame የቀረፀልን ህወሃት ነው። ጥያቄያችን ከመሬትና ከርስት በእጅጉ የላቀ ነው። ትግላችን ከሞት የተረፉት ወንድሞቻችን በነብስ እንዲቆዩ የማድረግ ነበር። በህይወት የመኖር አንገብጋቢ ትግል ነው የአካባቢው አማራዎች ያሳለፉት።የአማራ ህዝብ የተዋደቀውም ከመሬትና ከርስት በላይ የሆኑት የወልቃይት፣ የጠለምት፣ የጠገዴ እና የራያ አማራዎች ነፃ እንዲወጡ ነው። በእነዚህ አካባቢ የሚኖሩ የአማራ ህዝቦች በህውሃት ጭቆና ከሰውነት በታች እንዲሆኑ ተደርገዋል። ጭቆና የሚለው በራሱ አይገልፀውም። ስለዚህ ትግላችን ወገኖቻችንን ነፃ ማውጣት ነው። ሌላው ከወንድሞቻችን ነፃነት በሗላ የሚመጣ ነው።አሁን እነዚህ አካባቢዎች ነፃ ወጥተዋል። ነዋሪዎቹ አንገታቸውን ቀና አድርገዋል። ከዚያም አልፎ የሚበጃቸውን በአደባባይ እየገለፁ ነው። ነገም ወደሚፈልጉት ይሆናሉ። እኛም ከጎናቸው ሆነን እንደግፋቸዋለን።ያም ሆኖ የወልቃይትን እና የራያን ህዝብ የጨቆነው ህውሃት ብቻ አይደለም፤ እኛም ተጨምረን ነው ፍዳቸውን ያበዛነው። ለዚህም በተደጋጋሚ ይቅርታ እንጠይቃለን።(አቶ ገዱ አንዳርጋቸው – በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል በተካሄደው የባለሀብቶች መድረክ የተናገሩት)