December 5, 2020Konjit Sitotaw

The conflict in Ethiopia and TPLF’s ultra-nationalist ideology

While the rest of the country has embraced a new horizon, the TPLF continues to hold on to its old divisive ideology.

Mustafa Omer

‹‹ሕወሓት የዘራውን እያጨደ ነው››

ከጊዜ ኋላ ሲራመድ የነበረውና ከስህተቱ ለመማር ያልቻለው ሕወሓት በመጨረሻም የዘራውን መራራ ፍሬ እየሰበሰበ ነው አሉ፤ የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ዑመር፡፡ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በአልጀዚራ ላይ ባሰፈሩት ሀተታ እንደ ሕወሓት ያሉ ፓርቲዎች የመጨረሻ እጣ ፈንታም ከዚህ እንደማያልፍ ነው የጠቀሱት፡፡

Al Jazeera English

@AJEnglish

While the rest of the country has embraced a new horizon, the TPLF continues to hold on to its old divisive ideology. — writes Mustafa Omer for #AJOpinion.

The conflict in Ethiopia and TPLF’s ultra-nationalist ideology

The conflict in Ethiopia and TPLF’s ultra-nationalist ideologyWhile the rest of the country has embraced a new horizon, the TPLF continues to hold on to its old divisive ideology.aljazeera.com

1:30 AM · Dec 5, 2020

166 95 people are Tweeting about this

The conflict in Ethiopia and TPLF’s ultra-nationalist ideology

‹‹በኢትዮጵያ ያለው ግጭት እና የሕወሓት ከመጠን ያለፈ ብሔርተኝነት›› በሚል ርዕስ የወጣው የሙስጠፌ ጽሑፍ፤ ከሕወሓት አፈጣጠር ጀምሮ የነበሩ ብልሽቶችን ዳሷል፡፡ሕወሓት የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ በጋብቻ፣ በንግድ፣ በሃይማኖትና በባሕል እጅግ የተሳሰረ የመሆኑን እውነታ በመካድ የማይታረቅ ልዩነት እንዳላቸው አድርጎ ሲሰብክ ኖሯል ሲሉ ነው የከሰሱት፡፡ በዚህም አጥፊና ከፋፋይ የሆነውን ‹‹የእኛ እና እነሱ›› ትርክትን ፈጥሯል ይላሉ፡፡

ሀተታው ሲቀጥል የትግራይ ሕዝብ በጠላት እንደተከበበ አድርጎ በመስበክ በሚያስተዳድራቸው የመገናኛ ብዙኃን በኩልም ተከታታይ የጦርነት ዘጋቢ ፊልሞችን ሲያሳይ ስለመክረሙ አስታውሷል፡፡ሕወሓት ራሱን የብሔር፣ ብሔረሰቦች ሰላም ብቸኛ ጠባቂ አድርጎ ሲያስፈራራ መኖሩንም ነው ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ሙስጠፌ ያነሱት፡፡

Along the way, the TPLF developed its elaborate ideology, combining ultra-nationalism and ethnic pride with a sense of victimisation, especially directed at the feudal Amhara elite and the communists. It propagates the divisive idea of “us vs them”

that the Tigray people are surrounded by enemies and only the TPLF can ensure their protection and survival.

ሕወሓት ለዓመታት በበላይነት ይዞት የነበረውን የማዕከላዊ መንግሥቱን ሥልጣን በ2010 ካጣ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የተጀመሩ አገራዊ ማሻሻያዎችን ለመቀልበስ የሚችለውን ሁሉ አድርጓል ሲልም ጽሑፉ ይነበባል፡፡ በመላ አገሪቱ ግጭቶችን በተለያዩ መንግዶች ሲደግፍ እንደነበር በመክሰስ፤ በአገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ ኢትዮጵያ ሕግ ወደማስከበሩ ዘመቻ መግባቷንም ያስታውሳል፡፡

Amharic By አሐዱ ቴሌቪዥን