Image may contain: 1 person
Amhara Mass Media Agency

የወሰንና የማንነት ጥያቄዎች በሚነሱባቸው አካባቢዎች የዜጎች መብት ሊከበር እንደሚገባ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አቅጣጫ አስቀመጠ።ባሕር ዳር፡ ኅዳር 27/2013 ዓ.ም (አብመድ) የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት ባከሄደው መደበኛ ስብሰባው በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መክሮ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።የብጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም በሰጡት መግለጫ ስራአስፈጻሚው ከሃዲው የህወሃት ቡድን በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት ካደረሰና በአማራ ክልልም ትንኮሳ ካካሄደ በኋላ በተወሰደው የህግ ማሰከበር ዘመቻ እንደ ሀገር አኩሪ ገድል መፈፀሙ ተገምግሟል ብለዋል፡፡ ህወሃት እየተሸነፈ ሲሄድ እስካሁን ባለው 1 ሺ ንጹሃንን በማንነታቸው ለይቶ ገድሏልም ተብሏል፡፡የህግ ማሰከበር ዘመቻው በስኬት እየተጠናቀቀ ነው ያሉት አቶ ብናልፍ የቀረው መሪ ወንጀለኞችን ለህግ የማቅረብ ስራ በአፋጣኝ እንዲካሄድ ስራአስፈጻሚው አቅጣጫ አስቀምጧል ብለዋል፡፡የወሰንና የማንነት ጥያቄዎች በሚነሱባቸው አካባቢዎች ላይ ህወሃት በሃይል ማንነትን የመንጠቅ፣ ጥያቄውን የሚያቀርቡ አካላትን የመግደል፣ የማሰርና የማፈናቀል ስራ ሲሰራ ነበር፣ በዚህም ወደ 500 ሺ ዜጎች ተሰደዋል ያሉት አቶ ብናልፍ ጥያቄ አቅራቢወቹ ፍትህን ለ30 አመታት በሰላማዊ መንገድ ሲጠይቁ መቆየታቸውንና መብታቸውም መከበር እንዳለበት ስራ አስፈጻሚው መወያየቱን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ጥያቂያቸውን ህወሃት ባሰተናገደበት መንገድ ሳይሆን በሰላመዊ መንገድ ይመለሳል ምክንያቱም ነዋሪዎቹ መብታቸውን እንጅ የተለየ ስጦታ አልጠየቁም ነው ያሉት።የተፈናቀሉ ዜጎችን የማቋቋምና በከሃዲው ቡድን የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን ስራ ማስጀመር በትኩረት እንዲሰራ ስራ አስፈጻሚው ወስኗል፡፡ መሪ ወንጀለኞችን ለህግ የማቅረብ ስራ እየተሰራ ቡድኑን በሽብርተኝነት የመፈረጅ ስራው በጥናትና በነባራዊ ሁኔታዎች ታይቶ ይወሰናልም ብለዋል፡፡ ስራ አስፈጻሚው በሃገራዊና አለማቀፋዊ ዮፖለቲካ ሀይሎች ወቅታዊ አሰላለፍ ላይም መክሯል፡፡በሃገሪቱ ጽንፍ የወጡ አስተሳሰቦች እየተሰታወሉ ሀገር የማፍረስ አደጋ እንዳያመጡ የፖለቲካ ንቃት ላይ ይሰራል ተብሏል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገር ግንባታላይ በጎ አስተዋኦአቸውን እንዲወጡም ጥሪ ቀርቧል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአባይ ፖለቲካ ላይ የሚሰሩ ፕሮፖጋንዳዎች ላይ ያሉ ስጋቶችና መልካም ዕድሎች ተለይተው ውይይት ተካሂዶባቿል፡፡የብጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት ባከሄደው መደበኛ ስብሰባው በ2013 ዓ.ም ሀጋራዊ ምርጫ ፓርቲው የሚመራበትን የዘመቻ ሰነድም አጽድቋል፡፡ዘጋቢ: ዘመኑ ታደለ ከአዲስ አበባተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZበዌብሳይት amharaweb.comበቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ

ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m