1981 መጨረሻ ወይም 1982 ላይ ወልድያ በሔሊኮፕተር የተበተነው በአማርኛ እና በትግርኛ የተፃፈው (ካልተሳሳትኩ ሽፋኑ ቀይ ነው) መፅሀፍ የሚያስታውስ ሰው ይኖር ይሆን? በወቅቱ ለደርግ እጃቸውን ሰጥተው የነበሩት የትህነግ ከፍተኛ አመራሮች አብርሃም ያየህ እና ገብረመድህን አርአያ የሰጡት ቃለምልልስ የታተመበት ሲሆን ትህነግ ገና ከበርሃ እያለ ራያ እና ወልቃይትን ወደ ታላቋ የትግራይ ሪፐብሊክ እንዴት አድርጎ ለማካተት እንዳሰበ የሚያሳይ ነበር።

Desalegn HagereSelam

“ከታሪክ ዉጭ የሚደረግ እንቅስቃሴ መቅሰፍት ነዉ

“ከ30 ዓመት በፊት 1982 ዓ.ም ላይ ወያኔን ለቀዉ የወጡት የቀድሞ የቡድኑ ከፍተኛ አመራር የነበሩት የአድዋ ተወላጆቹ አቶ አብርሃም ያየህ እና ገብረመድህን አርአያ አሁን ዉዝግብ እየተነሳባቸዉ የሚገኙትን ቦታዎች አስመልክቶ በጋዜጠኞች ተጠይቀዉ ከመለሱት ላይ የተወሰደ ነዉ።

“በታሪክ የትግራይ ወሰን እስከ ሱዳን ነዉ የሚል ነገር የለም። የትግራይ ክልል በማንኛዉም ጊዜ ከሱዳን ጠረፍ ጋር የተያያዘ ነዉ የሚል ታሪክ ፈጽሞ የለም። ይሁን እንጂ ‘የትግራይን ሪፐብሊክ እንመሰርታለን’ በሚል ከጎንደር ወልቃይትን በመቁረጥ እስከ ሱዳን ድረስ እንዲሁም ከወሎ ሰቆጣን፣ አሸንጌን፣ አላማጣንና ቆቦን ወስዶ እስከ አሰብ ድረስ አዲስ ካርታ ተነድፏል። ይህ ካርታ ፈጽሞ በታሪክ የሌለ ከመሆኑም ሌላ አሁንም ሆነ ወደፊት ከአጎራባች ክፍላተ ሀገር ጋር የሚፈጥረዉ ችግር ከፍተኛ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ። የወሎንም ሆነ የጎንደርን መሬት የእኔ ነዉ ብሎ የሚነሳ ክፍል ከእነዚህ ሕዝቦች ጋር ከፍተኛ ቅራኔ መፍጠሩ የማይቀር ነዉ

“”ከታሪክ ዉጭ የሚደረግ እንቅስቃሴ መቅሰፍት ነዉ። ባጠቃላይ ይህ የትግራይ ካርታ ተብሎ የተነደፈዉ በጥቂት የቡድኑ አባላት ስሜት በመሆኑ ከታሪክ ውጭና በማንኛዉም ዘንድ ተቀባይነት የሌለዉ የቅዠት ሥዕል ነዉ።

እነዚህ ሰዎች የጎንደርንና የወሎን መሬት ቢፈልጉም በላዩ ላይ የሰፈረዉን ሕዝብ ፍላጎት ግን ማርካት አይችሉም። በዕዉነቱ በድርጊቱ በጣም አዝናለሁ። ከፍተኛ ቅራኔም ዉስጥ ይገባሉ”እነዚህ የቀድሞዉ የወያኔ ከፍተኛ አመራሮች እንግዲህ ይሄን ያሉት ወያኔ አዲስ አበባ ከመግባቱ ከአንድ አመት በፊት ነበር።