December 6, 2020

በትህነግ ፀጥታ ኃይልና በትግራይ ወጣቶች እንዲሁም በሺህ የሚቆጠሩ ንፁሃን የተጨፈጨፉባት ማይካድራ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ላይ ነች። የማይካድራ ከተማ ሕዝብ በትህነግ የፀጥታ ኃይል፣ በትግራይ ወጣቶችና ባለሀብቶች ለተጨፈጨፉት በሺህ የሚቆጠሩ ንፁሃን ጥቁር ለብሶ አስቧቸው አርፍዷል። ሰልፉ ጭፍጨፋውን በማውገዝ፣ በማንነት ላይ ያነጣጠረው ጥቃት እንዲቆምና በአማራ ላይ የተፈፀመው ጥቀት እውቅና እንዲሰጠው በመጠየቅ እየተካሄደ ነው። በተጨማሪም የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ማንነትና ርስት መብት እንዲከበር የሚጠይቅ ነው።