( የሚከተለውን ስጽፍ የአማራነት ፖለቲካን መደገፍ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ፡፡ የአማራነት፣ የትግሬነት፣ የኦሮሞነት .ፖለቲካ አሻጋሪ ፖለቲካ አይደለም፡፡ የዘር ፖለቲካ ፣ የዘር አወቃቀር፣ የዘር ሕገ መንግስት መታገድ አለበት የሚል ጠንካራ አቋም ነው ያለኝ፡፡ የኔ ማንነቴ ኢትዮጵያዊነቴ ነው)
የሕወሃት አሸባሪዎች በሰሜን ዕዝ መከላከያ አባላት ላይ የወሰዱትንና እና ወደ አማራ ክልል ዘልቀው በመግባት በስሮቃ ያደረጉትን ጥቅት ተከትሎ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል፣ የአማራ ክልል ሚሊሺያዎች ያደረጉትን አስተዋጾ ሁላችንም የምናውቀው ነው፡፡ ከዚያም የተነሳ በጉልበት ወደ ትግራይ ክልል ተጠቃለው የነበሩ ወልቃይት ጠገዴ፣ ራያ፣ ጠለምትና ራያ ከህወሃት ነጻ ሆነዋል፡፡ በነዚህ አካባቢዎች እነ ዶር ሙሉ ነጋ የማያዙት ጊዜያዊ መስተዳድሮች እየተመሰረቱ ነው፡፡
ያንን ተከትሎ አንዳንድ ወገኖች ደስተኛ አልሆኑም፡፡ በአማራ ክልል ያለውን ሁኔታ፣ የአማራው ማህበረሰብ ራሱን በማደራጀት፣ ራሱን በማስታጠቅ ህልዉናውን ለመጠበቅ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንደ ጸረ ኢትዮጵያዊነት፣ እንደ ዘረኝነት አድርገው ለማቅረብ ሲሞክሩ እያየናቸው ነው፡፡ አንዳንዶቹማ አብንን ከኦነግ ጋር፣ የአማራ ብልጽግናን ከኦሮሞ ብልጽግና ጋር የሚያመሳሰሉም አሉ፡፡፡እስቲ መረጃ ሳይኖራቸው እንዲሁ በጭፍን የአማራ ክልልና ከኦሮሞ ክልል የአማራ ብልጽግናንና የኦሮሞ ብልጽግናን፣ የአማራ ድርጅቶችን እና የኦሮሞ ድርጅቶች ለሚያመሳሰሉ፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያሉትን እጅግ በጣም ትላልቅ ልዩነቶች ለማሳየት ልሞኮር፤ ጥቂት ምሳሌዎች ነማስቀመጥ፡፡
የክልል/መሬት ባለቤትነትን በተመለከተ
=====================
የኦሮሞ ክልል ሕገ መንግስት የክልሉ ባለቤት ኦሮሞ ብቻ ነው ይላል፡፡ ያ ማለት ኦሮሞ ያልሆነው ማህበረሰብ በኦሮሞው ፍቃድ የሚኖር ፣ ሁለተኛ ዜጋ፣ ሰፋሪ፣ መጤ ተደርጎ ነው የሚወሰደው ማለት ነው፡፡ ጃዋር ከዚህ በፊት “ በኬኒያ ኢትዮጵያዊያኖች ይኖሩ የለም እንዴ ? በኦሮሚያ ኦሮሚያም መኖር ይችላሉ፡፡ ኦሮሞ አቃፊ ነው” እንዳለው፣ የኦሮሞ ክልል ሕገ መንግስት ኦሮሞ ያልሆኑትን እንደ ውጭ አገር ዜጎች ነው የሚያየው፡፡ወደ አማራ ክልል ስንመጣ የተለየ ሁኔታ ነው ያለው፡፡ የአማራ ክልል አንድ ቦታ ክልሉ የአማራ ነው አይልም፡፡ የክልሉ ባለቤት በክልሉ የሚኖሩ “ብሄር ብሄረሰብና ህዝቦች” እንደሆነ ነው የሚናገረው፡፡ ያ ማለት ምን ማለት ነው የአማራ ክልል የአማራ ብቻ አይደለም፡፡
በክልሉ የሁሉንም መብት በማክበር ረገድ
======================
በኦሮሞ ክልል በሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎች፣ ቀበሌዎች ከተማዎች የስራ ቋንቋ ኦሮምኛ ብቻ ነው፡፡ በቡራዩ ልዩ በአዳማ ልዩ ፣ በጂማ ልዩ ዞኖች ፣ በፈንታሌ፣ በግራር ጃርሶ ፣ በሎሜ ፣ በአቃቂና በመሳሰሉት ወረዳዎች፣ በአሰላ፣ በአዳማ፣ በጂማ፣ በቢሾፍቱ፣ በፍቼ፣ በወሊሶ፣ በሞጆ፣ በዱከም፣ በጣፎ፣ በሰበታ፣ በዝዋይ፣ በጎባ፣ በሻሸመኔ፣ በአርሲ ነገሌ በመሳሰሉት ከተሞች አማርኛ ተናጋሪዎች ነው የሚበዙት፡፡ሆኖም ግን ከሌላ ቦታ የመጡ አስተዳዳሪዎች ተሹመው፣ ሁሉም ነገር በላቲን/ቁቤ መጻፍ ስላለበት፣ ነዋሪው ገንዘብ ክፍሎ ሰነዶችን ከአማርኛ ወደ ላቲን እያስተረጎመ ነው አገልግሎት የሚያገኘው፡፡ ይህ አይነት ፍጹም ዘረኛና በአማርኛና በአማራ ጥላቻ ላይ የተመሰረተ አሰራር ነው ያለው፡፡
በአማራ ክልል አገዎች፣ አርጎባዎች፣ ኦሮሞዎች ራሳቸውን በራሳቸው ያስተዳድሩ በሚል ልዩ ዞኖችና ወረዳዎች ተደርጎላቸዋል፡፡ በቋንቋቸው ነው የሚማሩት፡፡ በዞንና በወረዳ ደረጃ በቋንቋቸው፣ አማራ ክልል ውስጥ ቢሆኑም፣ አገልግሎት ያገኛሉ፡፡ ከሚሴና ባቲ ያሉ የአማራ ክልል ከተሞች ብንሄድ፣ እዚያ ኦሮሞዎች በብዛት አሉ ስለተባለ፣ በኦሮሞኛ አገልገሎት ይሰጣል፡፡ ኦሮምኛ የወረዳዎች የስራ ቋንቋም ነው፡፡ አሁን የወልቃይትና የራያ አካባቢዎች ወደ አማራ ክልል ከተጠቃለሉም፣ በዚያ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች መብት ዙሪያ ብዙም የሚለወጥ ነገር አይኖርም፡፡ በትግሪኛ መማር፣ በትግሬኛ አገልግሎት የማግኘት አሰራርም ይዘረጋል ብዬ ነው የማስነው፡፡
አዲስ አበባና በተመለከተ
=============
የኦሮሞ ክልል መንግስት፣ የኦሮሞ ብልጽግና፣ የኦሮሞ ብሄረተኛ ፖለቲከኞች “አዲስ አበባ የኦሮሞ ንብረት ናት የሚል እምነት አላቸው፡፡ አዎን በዶር አብይ አህመድ የሚመራው የኦሮሞ ብልጽኛ በአዲስ አበባ ጉዳይ ኦነግ፣ ኦፌኮ፣ እነ ጃዋር እነሕዝቂለ ጋቢሳ ካላቸው አቋም የተለየ አቋም የለውም፡፡ ሁሉም አንድ ናቸው፡፡ ኦሮሞ በአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም ማግኝት አለበት፡ የሚል አጀንዳ ነው የሚያራምዱት፡፡ ባሌና ጊምቢ የሚኖረው፣ እንኳን አዲስ አበባ ሸዋን ረግጦ የማያውቀው ፣ አዲስ አበባ ተወልዶ ካደገው ይልቅ የባለቤትነት ስሜት ይሰማዋል፡፡
የአማራ ብልጽግና የአማራ ድርጅቶች፣ ምንም እንኳን በአዲስ አበባ ከ80% በላይ አማርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የሆነ፣ ከ55% በላይ ራሳቸውን አማራ ብለው የሚጠሩ ያሉባት ከተማ ብትሆኑም ፣ “አዲስ አበባ የአማራ ናት” ብለው አያውቁም፡፡ አማራ ልዩ ተጠቃሚ ይሁን አላሉ፡ም፡፡ አዲስ አበባ የነዋሪዎቿ ናት ነው የሚሉት፡፡ በአዲስ አበባ እኩል ተጠቃሚነት መኖር አለበት ነው የሚሉት፡፡
የዘር ፖለቲካ፣ የዘር አወቃቀርና የዘር ህግ መንግስትን በተመለከተ
==================================
የኦሮሞ ፖለቲከኞችና የኦሮሞ ድርጅቶች (የኦሮሞ ብልጽግናን ጨምሮ) አሁን ያለው ህወሃት የዘር አወቃቀርና ሕገ መንግስት እንዲቀጠል፣ ኦሮሞ፣ ኦሮሞ እያሉ በህዝብ ስም መሸጥና መለወጥ ነው የሚፈልጉት፡፡ የዘር ወይንም የብሄር ብሄረሰብ ፖለቲካ በህግ መታገዱን ይቃወማሉ፡፡ ከኦሮሞነት ውጭ ሌላ ነገር አይታያቸውም፡፡
ለነርሱ ኦሮሞነት አንደኛ ነው፡፡ ዘራቸው፣ ጎሳቸው፣ ጎጣቸው አንደኛ ነው፡፡
የኦሮሞ ክልል እንኳን አስነስ ወዳሉ ለአስተዳደር እመች ወደ ሆኑ፣ ህዝብን የበለጠ ወደ ሚጠቅሙ መስተዳደር እንድትቀየር ሊፈልጉ፣ ጭራሽ አዲስ አበባም ሃረር፣ ድሬዳዋ፣ ሞያሌን ዲላን የመሳሰሉትን ለመጠቅለልና ለመዋጥ ነው ፍላጎት ያላቸው፡፡ከዚህ ከዘር ፖለቲካውና አወቃቀሩ ጋር በተገናኘ እነርሱ በሚያስተዳድሯቸው ቦታዎች የተፈጠሩ የሩዋንዳ አይነት የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን እንኳን ማሰብ አልቻሉም፡፡ በሌላው ማህበረሰብ ላይ የደረሰው ትተን እንኳን፣ ከዘር ክልል ውዝግብ የተነሳ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ኦሮሞዎች መታወቂያቸው እየታየ ከሶማሌ ክልል መፈናቀላቸውን እንኳን አስበው፣ የዘር ፖለቲካን አደገኛነት መረዳት ያልቻሉ ጠባቦች ናቸው፡፡
የአማራ ፖለቲከኞች ከወሰድን፣ በአገር ደረጃ የዘር ፖለቲካ ቢታገድ፣ የዘር ሕገ መንግስትና የዘር አወቃቀር ቢቀየር፣ የአማራ አደረጃጀታቸው ለመተው፣ የአማራ ክልል አነስ ወዳሉ መስተዳድሮች ለመሸንሸን ፍቃደኛ ብቻ ሳይሆን ደስተኞችም ናቸው፡፡ወደ አማራነት ፖለቲካ የመጡት አማራነት አንደኛ ሆኖባቸው፣ ከኢትዮጵያዊነት በልጦባቸው ሳይሆን ተገደው፣ ራስን ለመከላከል በሚል ነው፡፡ ሁሉም ዘርና ጎጡን ትቶ፣ በፍቅር፣ በአንድነት፣ በመደመር ኢትዮጵያን ካለ፣ ከዚያ በላይ የሚፈልጉት ነገር የለም፡፡ ለነርሱ ኢትዮጵዖያዊነት አንደኛ ነው፡፡