December 9, 2020 – Konjit Sitotaw
ከመ/ር ታዬ ቦጋለ
ጉዳዩ የቁራጭ መሬት ወይስ የህልውና እና የማንነት?

* ማይካድራ እና ሁመራ የፈሰሰው ደም ቁራጭ ነውን?* የጅምላ ጭፍጨፋውና የጅምላ መቃብሩስ የቁራጭ መሬት ነውን?
* 30 ዓመታት በሙሉ በግፍ የተወሰደው መሬትና ማንነት ቁራጭ ስለሆነ ነውን?* ከሲዳማ ጋር በወንዶ ገነት፤ ከአላባ እና ስልጢ ጋር በአላጌ ኦሮሚያ የምትጣላው ቁራጭ መሬት ስለሆነ ነውን?* በሞያሌ እና በነጌሌ ቦረና ከሶማሊ ክልል ጋር እስከ ሪፈረንደም እና መገዳደል የሄድከው ቁራጭ መሬት ስለሆነ ነውን?
* አዲስ አበባ በኦሮሚያ መሬት ላይ ትንሽ ካሬ ሜትር ገባ ብሎ ኮንዶሚኒየም ሠራ ብለህ ትርምስ የፈጠርከው ቁራጭ መሬት ስለሆነ ነውን?!–
* ራያ ወልቃይትና ጠለምት 500ሺህ ሰው የተፈናቀለው ከቁራጭ መሬት ነውን?!* 10ሺዎች የተገደሉትስ ለቁራጭ መሬት ነውን?!
* ከኤርትራ በተቀማው፦ ባድመ ዛላንበሳ እና ፆረና 80ሺህ ወጣት ያለቀውስ?!
* እነእንትና፦ ሁለት ሰው ሞተ ብላችሁ መቀሌን በዕንባ እንዳላጥለቀለቃችሁ፤ ማይካድራ ላይ አንድ ከተማ ህዝብ በግፍ ተጨፍጭፎ ሳለ፤ ለምን ተለቀሰ ብላችሁ የምታላዝኑ ከአራጆቹ ጋር አንድና ያው ናችሁ።
=======================
በመጨረሻም ኢሬቻን በሚያህል ጠባብ ቦታ የወገኔ ደም ሲፈስ፦
“የፈሰሰው የኦሮሞ ደም _ ደሜ ነው”ቦሎ በአንድ ቀን ከባህርዳር እና ጎንደር _ ስለእኔ ከቃል አልፎ በተግባር የሞተልኝን የአማራ ወገን _ ደም የሚክድ ህሊና የለኝም። የታሠሩ የኦሮሞ አመራሮች መሪዎቼ ናቸው በማለት የተሰለፈውን አማራ በሀቁ እንድክደው የሚያደርግ አእምሮ አልተለጠፈብኝም።
—————————————–
‘በሬ ያላሰውን ወግቶ ያኮላሸውን ይቀርባል’ የሚለው ብሂል ለካ እብለት የለበትም!=======================
እንደኢትዮጵያዊ ብናስብ፤ እንደደረጃችን ብንመዝን ኖሮ የመከላከያው የአፋርና የአማራ ክንዶች እና የንፁሃን አማራዎች ደም ሳይደርቅ፤ በደማቸው ባልተሳለቅን ነበር። በእርታ ልርታ መንፈስ ጉዳዮቹ እንዲያልቁ አስታራቂ ሆነን በቀረብን ነበር። በእልህ የአማራውን ተጨማሪ ደም ለማስገበር የሚደረገው ሴራ ይሳካል ብላችሁ አታስቡ! መከላከያው ያልወጋውን፤ ያላረደውን የራሱን ወገን በጭራሽ ጣልቃ ገብቶ አይወጋም! የእናትህ ጡት ነው።