ፎርብስ ባወጣው 100 የዓመቱ (2020) ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ፕሬዘዳንቷ በ96ኛ ደረጃ ተቀምጠዋል።

የመጀመሪያዋ ሴት የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት የሆኑት ሳህለወርቅ፤ በዝርዝሩ የተካተቱ ብቸኛዋ አፍሪካዊ ናቸው።
ፎርብስ በድረ ገጹ “ለምክር ቤት ባደረጉት የመጀሪያ ንግግር ለሴቶች ድምጽ ለመሆን ቃል ገብተዋል” ሲል ገልጿቸዋል።
የፕሬዘዳንቷ መመረጥ ኢትዮጵያ ውስጥ በመጠኑም ቢሆን የሴቶች ውክልና እየጨመረ መምጣቱን እንደሚያሳይም ፎርብስ አስነብቧል።
በዝርዝሩ እነማን ተካተቱ?
በዝርዝሩ አንደኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት የጀርመኗ መራሔተ መንግሥት አንግላ መርከል ናቸው። መርከል በዝርዝሩ ለአስር ተከታታይ አመታት መሪነቱን ይዘዋል።

በዝርዝሩ ሲካተቱ ደግሞ ዘንድሮ ለ15ኛ ጊዜ ነው።
በሦስተኛ ደረጃ ላይ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዘዳንት ሆነው የተመረጡት ከማላ ሃሪስ ይገኛሉ።
የኒው ዚላንዷ ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደን ደግሞ 32ኛ ናቸው።
ይህ ዓመታዊ ዝርዝር ሲወጣ ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ መሆኑን የፎርብስ ድረ ገጽ ይጠቁማል።
በዘንድሮው ዝርዝር ከ30 አገራት የተውጣጡ ሴቶች ተካተዋል። ከእነዚህ መካከል አስሩ የአገር መሪዎች ሲሆኑ፣ 38ቱ ሥራ አስኪያጆች፣ አምስቱ ደግሞ በመዝናኛው ዘርፍ የተሰማሩ ሴቶች ናቸው።
በዝርዝሩ ከተካተቱት ሴት መሪዎች መካከል የኮሮናቫይረስ ስርጭትን መገደብ የቻሉ እንደሚገኙበት ተገልጿል።
ለሁለተኛ ጊዜ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው የተመረጡት ጀሲንዳ አርደን፤ በኒው ዚላንድ የመጀመሪያውን እና ሁለተኛውን ዙር ወረርሽን በብቃት መወጣት ችለዋል።
በ37ኛ ደረጃ የተቀመጡት የታይዋኗ ፕሬዘዳንት ሳይ ኢንግ ዌን፤ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለማግኘት ውጤታማ አሠራር ዘርግተዋል። 23 ሚሊዮን ሰዎች በሚኖሩባት ታይዋን በወረርሽኙ ሳቢያ ሕይወታቸውን ያጡት ሰባት ሰዎች ብቻ ናቸው።
የኖርዌይ ጠቅላይ ሚንስትር ኤርና ሶልበርግ (52ኛ) “ዴሞክራሲ ሰፍኖ ሰብአዊ መብት የተከበረባቸውና ሴቶች በማኅበረሰቡ ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ የደርሱባቸው አገራት ኮቪድ-19ን መዋጋት ችለዋል” ብለው ነበር።
በዝርርዝሩ ከተካተቱ መካከል በአምስተኛ ደረጃ ሜሊንዳ ጌትስ እና በሰባተኛ ደረጃ ናንሲ ፔሎሲ ይጠቀሳሉ።
ኦፕራ ዊንፍሪ በ20ኛ ደረጃ ተቀምጣለች።
ከመዝናኛው ዘርፍ ድምጻውያኑ ሪሀና (69) እና ቢዮንሴ (72) ይጠቀሳሉ።
አዲስ አበባ ተወልደው ያደጉት ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ የሁለት ወንድ ልጆች እናት ናቸው። ለዓመታት በዲፕሎማሲው ዘርፍ ሠርተዋል።
በወርሃ የካቲት 1942 የተወለዱ ሲሆን ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዘኛና አማርኛ አቀላጥፈው ይናገራሉ።
ከፈረንሳዩ ሞንተፔለ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ምሩቅ ሲሆኑ፤ እአአ ከ1989-1993 ተቀማጭነታቸውን ሴነጋል በማድረግ የማሊ፣ የኬፕ ቨርዴ፣ የጊኒ ቢሳዎ፣ የጋምቢያና የጊኒ አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል።
እአአ ከ1993-2002 ደግሞ በጅቡቲ አምባሳደር ሆነው የሠሩ ሲሆን፤ በወቅቱ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ቋሚ ተወካይም ነበሩ።
ከዚያም በመቀጠል ከ2002-2006 በፈረንሳይ አምባሳደር እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም ተወካይ ሆነው ሠርተዋል።
በኋላም በተባበሩት መንግሥታት ልዩ መልዕክተኛ ውስጥ የተቀናጀው የሰላም አስከባሪ ኃይል ተወካይ በመሆን በሴንትራል አፍሪካ (BINUCA) ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።
በአፍሪካ ሕብረት ውስጥና በተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚ ኮሚሽን ውስጥም የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ ሆነው አገልግለዋል። በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥም የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል ሆነው ሰርተዋል።
እአአ በ2011 የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ የነበሩት ባን ኪሙን፤ በኬንያ የተባበሩት መንግሥታት ዳይሬክተር ጄነራል አድርገው ሾመዋቸው አገልግለዋል።
በተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ በአፍሪካ ሕብረት ልዩ ተወካይ እንዲሁም በአፍሪካ ሕብረት የተባበሩት መንግሥታት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾመዋል።
ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ደግሞ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ሆነው እያገለገሉ ነው።
Forbes
#96 Sahle-Work Zewde
President, Ethiopia
Photo by Britta Pedersen/picture alliance via Getty Images
- In October 2018, Sahle-Work Zewde became Ethiopia’s first woman president and the only serving female head of state in Africa.
- A seasoned diplomat and veteran of the United Nations, Zewde was appointed with a unanimous vote by parliament.
- In her first address to parliament, Zewde promised to be a voice for women and stressed the importance of unity.
- The appointment joins a series of unprecedented shifts as part of Prime Minister Abiy Ahmed’s reforms focused on easing government control.
- Traditionally a ceremonial role, Zewde’s appointment is a tremendously symbolic move for the conservative country, opening the door for gender parity.
On forbes lists
#96 Power Women 2020
Stats
Age 70
Residence Ethiopia
Citizenship Ethiopia
Marital Status Married
Children 2