December 10, 2020

“ከፍ ወዳለ ተራራ ወጥተናል፤ ከዚህ መውረድ አይገባንም፤ ከዚህ ወደታች የምታወርዱን ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስቶች ወደ ታች እንድንወርድ የምትጎተጉቱን የፌስቡክ ሰዎች እባካችሁ ተውን”“ሰው ለሀገሩ የሚያለቅስበት ከፍታ ላይ ከደረስን ወደ ታች እንድንሄድአትመልሱን፤ ትልቅ ቦታ ላይ ነው አሁን የደረስነው፤ ኢትዮጵያ መጠኗ ምንድን ነው ልኳስ ምንድን ነው ቢባል ይሄው ነው”– ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 80ኛ አመት የምስረታ በአሉን አመቱን ሙሉ በተለያዩ መድረኮች እያከበረ ይገኛል። የበአሉ አካል በማድረግም በህግ ማስከበር ዘመቻው ላይ ለተሳተፉ የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች የምስጋና እና የውይይት መድረክ አካሂዷል።በዚሁ መድረክ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የስራ አመራር ቦርድ አባል ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ባደረጉት ንግግር፤ “ከፍ ወዳለ ተራራ ወጥተናል፤ ከዚህ መውረድ አይገባንም፤ ይህንን ከፍተኛ የሀገር ፍቅር ለበጎ እንጠቀምበት። ከዚህ ወደታች የምታወርዱን ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስቶች ወደ ታች እንድንወርድ የምትጎተጉቱን የፌስቡክ ሰዎች እባካችሁ ተውን። ሰው ለሀገሩ የሚያለቅስበት ከፍታ ላይ ከደረስን ወደ ታች እንድንሄድ አትመልሱን፤ ትልቅ ቦታ ላይ ነው አሁን የደረስነው፤ ኢትዮጵያ መጠኗ ምንድን ነው ልኳስ ምንድ ነው ቢባል ይሄው ነው” ብለዋል።–የህግ ማስከበር ዘመቻው ውጤታማ የሆነው መከላከያ አመራሩና ህዝቡ አንድ ላይ ተቀናጅተው በመስራታቸው እንደሆነ የጠቀሱት ዲያቆን ዳንኤል፤ “በሶስት አካላት ቅንጅት ያገኘነው ድል ነው፤ ከፊት መከላከያ ሰራዊት ተዋግቶ፣ ከመሀከል አመራሩ ሰርቶ፣ ከኋላ ደግሞ ህዝብ ደጀን ሆኖ የተገኘ ድል ነው። እነዚህ ሶስቱ ባይቀናጁ ኖሮ አደጋ ውስጥ እንገባ ነበር” ሲሉም ነው የገለጹት።–ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ያደረጉት ንግግር ዋና ዋና ሃሳቦችም እንደሚከተለው ቀርበዋል፤👉 ኢትዮጵያ ውስጥ ሶስት አካላት በደንብ የተቀናጁበት ወቅት ነው፤ ህዝብ፣ መሪና መከላከያ፤ ስለዚህ ሁሌም እትዮጵያ እንደዚህ ነው መሆን ያለባት፤👉 ኢትዮጵያ እንዴት ነው መኖር ያለባት ከተባላ እንዳለፈው አንድ ወር ነው፤👉 ህዝብ፣ መሪና መከላከያ ለአንድ ዓላማ ከሰራን ይቺ ሀገር መድረስ የማትችልበት ነገር የለም፤ በጣም አደራ የምለው ሶስቱንም ይዘን ነው መቀጠል ያለብን፤👉 ከፍ ወዳለ ተራራ ወጥተናል፤ ከዚህ መውረድ አይገባንም፤ ይህንን ከፍተኛ የሀገር ፍቅር ለበጎ እንጠቀምበት፤👉 ከዚህ ወደታች የምታወርዱን ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስቶች ወደ ታች እንድንወርድ የምትጎተጉቱን የፌስቡክ ሰዎች እባካችሁ ተውን፤ ከፍታው በጣም ደስ ስላለን አታውርዱን፤👉 ሰው ለሀገሩ የሚያለቅስበት ከፍታ ላይ ከደረስን ወደ ታች እንድንሄድ አትመልሱን፤ ትልቅ ቦታ ላይ ነው አሁን የደረስነው፤ ኢትዮጵያ መጠኗ ምንድን ነው ልኳስ ምንድ ነው ቢባል ይሄው ነው፤👉 በትልቅ የእግር ኳስ ሊግ የሚጫወትን ቡድን ውረድና ከጤና ቡድን ጋር ግጠም ቢባል የፈለገውን ብር እንስጥህ ቢሉት አይወርድም፤ ይቅር ይላል እንጂ አያደርገውም፤ እንኳን ለመጫወት ተመልካች ለመሆን እንኳን ፍቃደኛ አይሆንም፤ እኛም እዛ ከፍታ ላይ ስለሆንን እንኳን ተጫዋች ለመሆን ወርደን ተመልካች ለመሆን መፍቀድ የለብንም፤👉 ኢትዮጵያ 24 ስዓት የሚሰሩ ብዙ ልጆች አሏት፤ በሚዲያው ላይ የሚሰሩት ጋዜጠኞች ወጣቶች ናቸው ኢትዮጵያም በጣም ዕድለኛ ናት፤ ወደ 70 የሚጠጉ ጋዜጠኞች ወደ ግንባር ዘምተዋል፤ በእነዚህ ወጣቶች ልብ ውስጥ ኢትዮጵያ ከተቀረፀች በቂያችን ነው ብዬ አምናለሁ፤👉 አደራ የምለው ከዚህ በምንም መልኩ መውረድ የለብንም፤ ይህንን ነው እየመነዘርን ለልማት፣ ለኢኮኖሚ፣ ለማህበራዊ ዕድገት፣ ለሰላምና ለአንድነት መጠቀም ያለብን፤