December 15, 2020

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ብልፅግና የአማራ ብልፅግና ላይ ክስ አቀረበ፡፡
አሻራ ሚዲያ
ታህሳስ 6 2013 ዓም ባህር ዳር
የቢሻንጉል ጉምዝ ብልፅግና የአማራ ብልፅግና ልውረረህ እያለኝ ነው ብሏል፡፡ ከዚህ ቀደመም የቢሻንጉል ጉምዝ ብልፅግና ቻግኒ፣መተማ እና ጃዊ የቢሻንጉል ናቸው ብሎ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡
የቤኒሻንጉል ብልፅግና ያሶ ወረዳን ለኦሮሚያ ብልፅግና ያስረከበ ሲሆን፣ መተከልንም ለኦኀግ ለማስረከብ እየሰራ እንደሆነ ይነገራል፡፡
እስካሁን ከ60 ሺ በላይ አማራዎች ብልፅግና ከተመሰረተ ወዲህ የተፈናቀሉ ሲሆን፣ ይሄ ሁሉ መፈናቀል እና ግድያ ሲደርስ ሀላፊነቱን መወጣት ያልቻለው ክልል ዛሬ ላይ ራሱን ከሳሽ ሆኖ ተነስቷል፡፡
የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ሀላፊ አቶ ግዛቸው የቢሻንጉል ጉምዝ መንግስት ሀላፊነቱን እየተወጣ አይደለም ያሉ ሲሆን፣ፖሊስ ኮሚሽነሩም አቶ አበረ አዳሙም በቢሻንጉል የሰው ስጋ እየተበላ ህግ አልተከበረም ብለዋል፡፡
ይሄ ሁሉ ሲሆን የፌዴራል መንግስት ወሳኝ መፍትሄ ማቅረብ ሲሳነው ተስተውሏል፡፡
ብልፅግና አንድነት የሌላቸው ፓርቲዎች ጥርቅም እንደሆነ የቤኒሻንጉል፣የአማራ እና የኦሮሚያ ብልፅግናዎች በሚያነሱት ሀሳብ መረዳት ይቻላል፡፡
በዚህ ሁሉ መሃል የአሻራ የመረጃ ምንጮች እንዳረጋገጡት በመተከል እና ወለጋ አማራ በጅምላ እየተገደለ እና እየተፈናቀለ ነው፡፡
ብልፅግና ሰክኖ ሀገር ከመምራት ይልቅ እርስ በእርሱ እየተሻኮተ ኢትዮጵያን የንፁሃን ደም ማፍሰሻ አድርጓታል፡፡