December 17, 2020

በትግራይ ከጁንታው ጋር ተሰልፎ የነበረው የኦነግ ሸኔ አባል ….. የኦነግ ታጣቂዎች ከጁንታው ጋር አብረው ተሠልፈው የነበረ ሲሆን፤ እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት መስጠታቸው ተረጋግጧል

Image may contain: 1 person

(ኢ.ፕ.ድ) -ፈይሳ ተካ ይባላል፡፡ የ22 ዓመት ወጣት ነው፡፡ ትውልድና እድገቱ በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ሸዋ ዞን ግንደ በረት ከተማ ነው፡፡

ትምህርቱን ከስምንተኛ ክፍል አቋርጦ ሀገራችንን ነጻ እናውጣ እያለ በሚሰብከው ታደሰ ጆንሴ በሚባል ሰው አማካኝነት ለኦነግ ሰራዊትነት ተመልምሎ ጊንጪ አካባቢ ጭልሞ በምትባል ቦታ ከጥር 2012 ዓ.ም ጀምሮ ከ26 ባልደረቦቹ ጋር ስልጠና እንደወሰደ ይናገራል፡፡

ከስልጠና በኋላም ሁሉም ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመለሱና ስልክ ሲደወልላቸው የሚፈለጉበት ቦታ ድረስ እንዲመጡ ትእዛዝ ተሰጣቸው፡፡ እንደተባለውም የሰሜን እዝ ሰራዊት ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ አስቀድሞ ማንነቱን በማያውቀው ሰው አማካኝነት ስልክ ተደወለለት፡፡በተባለው ቦታ ተሰባሰቡና ጉዟቸውን ወደ ትግራይ አደረጉ፤ በእግርም በተሸካርካሪም ከተጓዙ በኋላ ጨርጨር አካባቢ ከትግራይ ታጣቂዎች ጋር ተቀላቀሉ፡፡

ፈይሳ ተካ ስም ተቀየረለትና የትግል ስሙ ብሩክ ተካ ሆነ ፡፡ ምግብና ትጥቅ ተሟላላቸው፤ በወር ከስድስት ሺህ እስከ ሰባት ሺ ብር እንደሚከፈላቸውም ተነገሯቸው ወደጥቃት እንዲገባ ስምሪት ተሰጠው፡፡

ከጥቂት ቀናት በኋላ በሰሜን እዝ ሰራዊት ላይ ጥቃት እንዲፈጽሙ ትእዛዝ ተሰጥቷቸው እንደነበርና እርሱ ግን አለመሳተፉን ፈይሳ ይናራል፡፡ አመራሮች የትግሉ ዓላማ ሀገሪቱን ነጻ ለማውጣት እንደሆነ ይነግሯቸው እንደነበረር ይገልጻል፡፡

ቃል የተገባላቸውን የወር ደመወዝ ሲጠይቁ ግን መንግስት የኢኮኖሚ ምንጮችን ስለዘጋብን መክፍል አንችልም የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ፈይሳ ይናራል፡፡ መከላከያ ሰራዊት ህግን የማስከበር ርምጃ ሲጀምር ፈይሳ እጁን በሰላማዊ መንገድ ሰጥቷል፡፡ በማያውቀው ነገር በሰዎች ተታሎ በጥፋት ዓላማ ውስጥ መሳተፉ እንደጸጸተው ፈይሳ ገልጾልናል፡፡

እንደ ፈይሳ ሁሉ በርካታ የኦነግ ታጣቂዎች ከጁንታው ጋር አብረው ተሠልፈው የነበረ ሲሆን፤ እጃቸውን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት መስጠታቸውን በስፍራው የሚኘገው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ አረጋግጧል።

Image may contain: 2 people, people standing and outdoor