የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገራዊ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤቶች ምርጫ ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 ቀን 2013 ዓ·ም እንደሚሆን አስታውቋል።
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔ ድምፅ መስጫ ቀን ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ/ም እንዲሆን ዛሬ ይፋ ባደረገው ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው አሳውቋል።
ይህ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ የትግራይ ክልልን አያካትትም ተብሏል።
የምርጫ ቢሮዎች መከፈት የክልል መስተዳድር አባላት ከፍተኛ ትብብር ስለሚያስፈልገው፤ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ይህንን ድጋፍ ለማድረግ ጊዜ ስለሚያስፈልገው እንዲሁም በክልሉ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለምርጫ በሚስማማ መልኩ መመቻቸቱ ሲረጋገጥ በክልሉ የሚደረገው ምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ቦርዱ የሚያሳውቅ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 28 እንዲሆን በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው ላይ አሳውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ እና የድሬደዋ ከተማ መስተዳድር የድምጽ መስጫ ቀን ሰኔ 5 መሆኑን ገልጿል።
