
ለምን???? የፍ/ቤት ዳኞችን…“እናውቃለን እናንተም የመንግስት ተለጣፊዎች ናችሁ÷ የመንግስት አገልጋዮችም ናችሁ÷ በዚህ ችሎት መዳኝት በራሱ ውርደት ነው።”( እስካለ ደምሌ ከችሎት)
የዛሬው ችሎት የተሰየመው አቃቤ ህግ ያሻሻለውን ክስ በማየት የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለማድመጥ በሚል ነበረ።የዛሬውን ችሎት ለመከታተል ልደታ ፍ/ቤት የተገኘው የአዲስ አበባ ወጣት ለጉድ ነበር።
ምንም እንኳን ለመታደም ከተገኙት ውስጥ ጥቂቶቻችን እንድንገባ ቢፈቀድም……ዳኞች የተሰየሙት የእምነት ክህደት ቃል ለማድመጥ እንደሆነ ጥቅሰው በቀጥታ አንደኛ ተከሳሽ የሆነውን እስክንድር ነጋ ቃሉን እንዲሰጥ ጠየቁ….ከዛ በፊት ግን አንድ የሚለው ነገር እንዳለና እንዲፈቅዱለት በፍፁም ትህትና ፍ/ቤቱን ጠየቀ። ምላሻቸው ግን አምቢታ ነበር።የግራ ዳኛ”ወንጀሉን ፈፅመሀል ወይስ አልፈፀምክም ?” ጠየቀች! እስክንድር! ” አልፈፀምኩም።”
የግራ ዳኛ ” አሁን መናገር የምትፈልገውን ቀጥል!”
አስክንድር ቀጠለ…..”አሁን የምናገረውን እባካችሁ ለታሪክ እንዲቀር ስለምንፈልግ ፍ/ቤቱ በድምፅ እንዲቀዳለኝ አልያም ቃል በቃል እንዲመዝግብልኝ በትህትና እጠይቃለኹ” !
በድምፅ እንደማይቀዳ ዳኞች ገልፀው ÷ ቃል በቃል ከቻሉ እንደሚመዘግቡት ተናገሩ።
እስክንድር ቀጠለ….“ከሁሉም በፊት …ሁሉን በሚያየውና ሁሉን በሚሰማው እዚህ ተከሰን ችሎት ፊት የቆምነው አራታችንም ንፁህ መሆናችንን እገልፃለሁ።ጥፋተኛ ብቻ አይደለንም ሳይሆን …ይህ ክስ አንድም ዕውነት የለበትም።
ሁሉንም በማታዩት በፍ/ቤቱ: በህዝብና በታሪክ ፊት ግን እውነት ዘግይቶም ይሁን ፈጥኖ እንደሚወጣና ነፃ እንደሚያደርገን አምናለሁ።”
ሁለተኛ ተከሳሽ ስንታየሁ ቸኮል….
“ወንጀል አልፈፀምኩም÷ ይህ ብቻ ሳይሆን ህዝብን የስልጣን ባለቤት እንዲሆን እየለፋን ባለንበት ሁኔታ ተረኝነት የተጠናወተው መንግስት በምርጫ እንዳንሳተፍ ሲል ፍፁም የውሸት ክስ አዘጋጅቶ ነው ያሰረን።”
ሶስተኛ ተከሳሽ አስቴር ስዩም….….
”ወንጀሉን አልፈፀምኩም…
በወደቀው ስርዕትም በተመሳሳይ ችሎት ስለምን ስለ ዜጎች እኩልነት ..ፍትህ ..ለነፃነት ..ለዴሞክራሲና ለአንድነት ታገልሽ ተብየ …እንደ እናንተ በተሰየሙ ዳኞች የውሸት ተፈርዶብኝ እስር ቤት ብዙ ማቅቂያለሁ ። ይሁን እንጅ በዚህ አላፍርም ኩራት ይሰማኛል።አሁንም ያው ነው የለመድኩት ውሸት… እንኳን ወንጀል ልንፈፅም ቀርቶ ….ባጠቃላይ ክሱ እንዲህ ነው….
~ የብሔር ባላንስ(ሚዛን) ክስ
~ የፍትህ ስርዓቱን የናቀና ያጋለጠ ክስ~ህዝቡን እና ዜጎችን ያዋረደ
~ ሰብዓዊነትን የጣሰ~ የፖለቲካ ክስ እና~ አቃቤ ሕግ የስርዓቱ ቡችላ በመሆኑ ብቻ የተደረገ ነው።”በስተመጨረሻ ዳኞች አደራ የምላችሁ እና በእግዚአብሔር ስም የምጠይቃችሁ ነፃ ሆናችሁ እንድትዳኙን ነው ። አመሰግናለሁ!”
አራተኛ ተከሳሽ አስካለ ደምሴ…………
”ወንጀሉን አልፈፀምኩም÷ በሀሰት ነው የተከሰስኩት… እኔ የመንግስት ሰራተኛ ነኝ….የተከሰስኩት ስለምን የመንግስት ደምወዝ እየወሰድሽ ለባልደራስ ትሰሪያለሽ በሚል ነው….ይልቁንስ ከፓርቲው ከወጣሽ ኮንዶሚኒየም እንሰጥሻለን÷አመራር ትሆኛለሽ÷ ለትምህርት ወደ ውጭ አገር እንልክሻለን የሚሉ ማባበያዎች ይቀርቡልኝ ነበረ….ይሁን እንጅ እምቢ እኔ የምታገለው ተረኝነትን ነው…ለእኩልነት እና ለፍትህ ነው በማለቴ ብቻ ነው የአርቲስቱ ግድያ ከተፈፀመ ከ42 ቀናት በኋላ ከስራ ቦታ አፍነው የወሰዱኝ….ስለሆነም ባስቸኳይ ፍትህ ፍትህ ፍትህ እንዲሰጠን እጠይቃለሁ።ፍ/ቤቱ የዕምነት ክህደት ቃል አዳምጦ ጨረሰ። አቃቤ ህግ ቀጠለ… “ምስክሮች በዝግ ችሎት እና ከመጋረጃ በስተጀርባ እንዳይደመጡ ቀደም ሲል ፍ/ቤቱ የወሰነውን ውሳኔ ተቃውመን ይግባኝ ብለናል….በመሆኑም የክሱ ቀጠሮ ይራዘምልን!” ጠየቀ!እስክንድር በመሃል አቋርጦ ገባ…”ይግባኙ ሂደቱን ቀጥሎ መጓዝ ይችላል ግን እኛ በቀጣዩ አገራዊ ምርጫ በህዝብ ካርድ መዳኘት ስለምንፈልግ ፍትህ በቶሎ ይሰጠን! አሁንም ጊዜውን ሆን ብሎ አቃቤ ህግ ማራዘም ስለፈለገ ነው ይህንን ጥያቄ ያነሳው…ከተቻለ በ1998 ዓ.ም እንደተደረገው በየለቱ ጉዳያችን ይታይ!”
ይህን ተናግሮ እንደጨረሰ ፍ/ቤቱ በተሰየሙት ዳኞች በኩል(ግራ ዳኛዋ) ከላይ ተፅፎ በትንሽየ ማስታወሻ ከፊት ለፊት የተቀመጠውን ማስታወሻ ገለጥ በማድረግየግዜ ቀጠሮውን…..ማለትም የመጀመሪያ ዙር ምስክሮችን ለማሰማት በሚል …መጋቢት 29 ቀን (ከ4 ወር በኋላ) ቀጠሩት ። ይህን ጊዜ በቅፅበት ተከሳሾችም ችሎቱን የታደሙ የአዲስ አበባ ወጣቶችም ከፍተኛ የተቃውሞ ጩኸት አሰሙ። ፖሊስ ወጣቶችን አስገድዶ ከችሎት እንዲወጡ አደረገ።
ተከሳሾች ፍትህ …ፍትህ እያሉ ጮሁ..በኢትዮጵያ ለእርሷ ሲሉ ለተሰውት፣ ደማቸው በፈሰሰው እያሉ ተማፀኑ በዚህ ሂደት ዳኞች “ችሎቱን ጨርሰናል ” በሚል ሾልከው በገቡበት በር በፖሊስ ታጅበው ሾልከው ወጡ። እነ አስክንድር ዕውነት ደግሞ በካቴና ገባች።እነ እስክንድርም በፍትህ ስርዓቱ መሞት አዝነው ከአዳራሽ ሲወጡ …በድንገት ለደቂቃዎች ያላቋረጠ ከፍተኛ ጭብጨባና ፉጨት የተቀላቀለበት ድጋፍ ተቀበላቸው( አዲስ አበቤዎች ነበሩ)።በዚህ የተደናገጡት ጥበቃዎች የአዲስ አበባ ወጣቶችን እየገፈተሩና በጠብ መንጃ እያስፈራሩ አስወጧቸው። አበቃ!በወግደረስ ጤናውፍትህ!!ታህሳስ 16 2013 ዓ.ምተረኝነት በቃ!!
