December 28, 2020

‘My country in trouble’: WHO chief on Ethiopia’s Tigray conflict

Tedros, the most high-profile Tigrayan, says he has many relatives in the troubled region, ‘including my younger brother’.

ቴድሮስ አድሐኖም ወዳጆቼና ዘመዶቼ በትግራይ ውስጥ ችግር ላይ ናቸው ሲሉ አማረሩ

አገሬ በችግር ላይ ነች ሲሉ የሕወሓት ማእከላዊ ኮሚቴና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ኃላፊ በትግራይ ውስጥ በተከሰተው ሂደት ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ዶክተሩ ታናሽ ወንድሜን ጨምሮ በርካታ ወዳጆቼ በችግር ውስጥ ናቸው ሲሉ ለሕወሓት ጓዶቻቸው ያላቸውን ጭንቀት በጤና ድርጅቱ መድረክ ላይ ይፋ አድርገዋል።

በአለም የጤና ድርጅት ሀላፊ ቴድሮስ አድሃኖም ገብረየሱስ በግል አስተያየታቸው በኢትዮጵያ ውስጥ እየተባባሰ ስለመጣው ግጭት የግል ሕመም ሆኖብኛል ሲሉ ተናግረዋል።

በተባበሩት መንግስታት የጤና ኤጄንሲ የመጨረሻ የዜና ኮንፈረንስ ላይ ዶክተሩ እንደተናገሩት ከ ‹ኮቪድ› በተጨማሪ 2020 አገሬ በችግር ላይ ስለነበረች ለእኔ በጣም ከባድ ሆኖብኝ ነበር ብለዋል።በትግራይ ክልል ውስጥ ብዙ ወዳጆችና ዘመዶች እንዳሏቸው የተናገሩት ቴድሮስ ታናሽ ወንድሜን ጨምሮ ፣ የት እንዳሉ አላውቅም ሲሉ ገልጸዋል።

READ MORE – https://www.aljazeera.com/news/2020/12/28/personal-pain-who-chief-speaks-on-ethiopias-tigray-conflict