በ መኮንን ተስፋዬ እንደፃፈው
ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀርአኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!
ሲሳይ የሺጥላ ማን ነው ??

…በ ወንድሙ ሰርክአዲስ የሺጥላ እንደተነገረው፤………ስለ ሲሳይ የሺጥላ ተጨማሪ መረጃ ያላችሁ አንባቢዎቼ ብታጋሩኝ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው።
ሲሳይ የሺጥላ ከ አባቱ ከሻለቃ የሺጥላ አበበ እና ከ እናቱ ወ/ሮ ተዋበች ተመስገን በ 1951ዓ.ም በሐረር ከተማ ተወለደ። እድሜውም ለትምህርት ሲደርስ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርቱን ሐረር በሚገኘው ራስ መኮንን አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከተማረ በኋላ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በሐረር መድሃኒዓለም ገብቶ ተከታትሏል። ሲሳይ የሺጥላ በትምህርቱ በጣም ጎበዝ ከመሆኑም በላይ በጓደኞቹና በአካባቢው በጣም የተወደደ ወጣት ነበር።
በ ኢሕአፓ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ የነበረው ሲሳይ የሺጥላ፤ የቅስቀሳ ፅሁፎችን ይዞ ከሐረር ባቢሌ በአውቶቡስ ለመጓዝ ሲነሳ ሐረር ኬላ ላይ በነበረ ጥብቅ ፍተሻ ተይዞ ወደ መምርያ ፖሊስ ጣብያ ተወስዶ ለእስር ይዳረጋል። ከሁለት ሳምንት በኋላ ወደ አራተኛ ፖሊስ ጣብያ ተወስዶ ብዙም ሳይቆይ በ 5/12/1969 በደርግ ወንጀለኞች ተገደለ።ክብር የህዝብን ጥያቄ አንግቦ ግንባሩን ለጥይት ለሰጠ ጀግና ትውልድ!!ለህግ የበላይነት፤ ለሰላም ለዴሞክራሲና ለ እኩልነት..
ሁሉንም ያካተተ የሽግግር መንግስት!!!
የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል