ታላቅ ህዝባዊ መድረክ በራያ
ወሎ!
ወሎ የደጋጎች ሀገር፣
ወሎ የታሪክ ማህደር
ራያ አላማጣ የጀግኖቹ መንደር፤
ራያ አላማጣ፣ጨርጨር እና ኦፍላ የጀግኖቹ መንደር።
ራያ እና ቆቦ፣ ጨርጨር እና ኮረም፣ ኦፍላ እና ሰቆጣ፣ጎንደር እና ዳንሻ፣ ወልቃይት ጠገዴ፣በጀግናው ሰራዊት በልዩ ሀይላችን፣ በጀግናው ሚሊሻ ከአፈና ወጥተዋል ከትሕነግ ወንበዴ።
ራያ እና ጨርጨር፣ኮረም አላማጣ ታሪክንና ወጉ፣
ባህልና ፍቅሩ ወደነበረበት ይመለስ በህጉ።
ራያ አላማጣ ታጥሮ የነበረው የሰንሰለት አጥር፣
ተነቃቅሎ ወድቋል በህግ ማስከበር።
እንግዲህ ራያ በአንድ ላይ ሆነን፣
በፍቅር በሰላም እየተወያየን፣
ልማት ልናመጣ ወጣቱን ይዘን።
ወሎ ራያ ቆቦ ጨርጨር አላማጣ
ታሪኩ ብዙ ነው፣ደንበሩ ሰፊ ነው፤
ይጽደቅ እንደገና፣
ከተቀበርክበት ዛሬ ተነስተሃል በልደት በገና።
ወይ ውርደት ወይ ቅሌት(2)፣
ይሄ የህወሃት መሪ፣
ልማት መስራት ትቶ ምሽግ አስቆፋሪ።
ሁለት አመት ሙሉ የተሰራው ምሽግ፣
አንድ ወር ሳይሞላ ተበታትኖ በኗል
እንደ ኩበት አመድ።
ወልቃይት ጠገዴ፣ ዳንሻ እና ሁመራ፣
በጀግናው ልጆችህ ነጻ ወጥተሃል፣
መሬትህን አርሰህ ሰርተህ ልትበላ ይዘሃል።
ኩራ በልጆችህ ነጻነትህ ደምቋል፣
ከስቃይ መከራ።
ጎንደር እና ጎጃም የጀግኖቹ መንደር፣
የቴዎድሮስ ሀገር፣ የበላይ ዘለቀ፣
ሀሳቡ ተሳክቷል ትግሉ የደመቀ።
ጨለማው ተገፎ ብርሃን አግኝተናል።
እጅግ የደመቀ።
ራያ የማን ናት? ራያ ወሎ ናት!።(2)
ይህ ነው ምስክሩ እኛ እንደምናውቃት።
የአላማጣ “ህዝቦች”፣የጨርጨርም ህዝቦች
በጣም ተደሰቱ እስከ ዘላለሙ፣
ዛሬ ተገናኝተን ስለተወያየን ወንድም ከወንድሙ።
ስላዳመጣችሁ አመሰግናለሁ፤
ከራያ ጥሙጋ ጎብዬ ከተማ አለሙ እባላለሁ።

ከ30 አመት በኋላ በራያ የተደረገው ህዝባዊ መድረክ- አሚማ መረጃhttps://www.gofundme.com/f/amc-support-2020?utm_source=customer&