
ጃንዩወሪ 29, 2021
- ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል፦ በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር ቶማስ ግሪን ፊልድ
ዋሺንግተን ዲሲ — በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር ቶማስ ግሪን ፊልድ በኢትዮጵያ ያላው የሰብዓዊ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን መሆኑን ገለፁ።
አምባሳደር ግሪንፊልድ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳዮች ሴኔት ኮሚቴ የእጩዎች መስማት ሂደት ላይ የኢትዮጵያን ጉዳይ በተመለከተ ተጠይቀው፤ “በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳስቦኛል። ከሦስት ዓመት በፊት ይቺን አገርና አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትሯን እያከበርን ነበር። ወደፊት የመራመድ ዕድል ስለገጠማቸው ለሕዝባቸው ብልፅግና የሚያመጡበት ጊዜ ነው ብለን ደስ ብሎን ነበር። አሁን ከራሳቸው ሕዝብ ጋር ጦርነት ላይ ናቸው። የተባበሩት መንግሥታት ሁኔታውን ቀረብ ብሎ አይቶ እንዴት ምላሽ መስጠት እንዳለበት ማየቱ አስፈላጊ ነው።” ብለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

አምባሳደር ቶማስ ግሪን ፊልድ በትግራይ ክልል ያለው የሰብዓዊ ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ገለፁ
By ቪኦኤ
