On Feb 1, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብርጋዴል ጄነራል መአሾ ሀጎስ ስዩም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ተልእኮ አዛዥ ሆነው ተሹመዋል፡፡

ብርጋዴር ጄነራል መአሾ ሀጎስ ስዩም በኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ ለ25 ዓመታት እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የላይቤሪያ ፣ ዳርፉር ሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ ማገልገላቸውም ታውቋል። ሹመቱም ከጥር 4 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደተሰጣቸውም የተመድ መረጃ ያመላክታል፡፡

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/