February 1, 202

ዉይይት፤ የህወሓት ከፖለቲካ መድረክ መሰረዝ ተስፋ ወይስ ተግዳሮት? 

DW : 6ኛዉን ብሔራዊ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ በምትገኘዉ ኢትዮጵያ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ «ህወሓትን» ከፖለቲካ መድረክ መሰረዙን አስታዉቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቅርቡ እንዳስታወቀው የሕወሃትን የፓርቲነት ህጋዊ ሰውነት የሰረዘው አመፅ ላይ መሣተፉን በመረጋገጡ ነዉ።

ቦርዱ የፓርቲዉ ኃላፊዎችም ይሁን ተወካዮች በፓርቲው ስም መንቀሳቀስ አይችሉም ሲልም ውሳኔዉን አሳልፏል። 6ኛዉ ብሔራዊ ምርጫ ትግራይን አይጨምርም ። ይሁንና ለትግራይ አዲስ የምርጫ መረሃ-ግብር እንደሚወጣ ምርጫ ቦርድ አሳዉቋል።

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሃት) ባለፉት 47 ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ በአሉታዊም ይሁን በአወንታዊ መልኩ ተፅዕኖ ሲፈጥር የቆየ አንጋፋ የፖለቲካ ድርጅት ሲሆን፤መሰረቴ ነው በሚለው የትግራይ ክልልም ቀላል የማይባል ደጋፊ እንዳለውም ይነገራል።

ፓርቲዉ ብዙ ችግሮች ቢኖሩበትም በኢትዮጵያ ጠንካራ የአስተዳደር መዋቅር በመዘርጋትና ሕዝብን በማደራጀት የተሻለ አቅም ነበረው፤ የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህወሓት ላይ ያሳለፈዉን ዉሳኔ የሚቃወሙ እንዳሉ ሁሉ ፤ የህወሓት መሰረዝ እጅግ ዘግይቶአል ሲሉ አስተያየቶቻቸዉን የሚሰጡ አሉ። የህወሓት ከኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ መሰረዝ ተስፋ ወይስ ተግዳሮት?

የእለቱ የዉይይት ርዕሳችን ነዉ።

በዚህ ዉይይት ላይ እንዲሳተፉ የጋበዝናቸዉ ፤

አቶ ግርማ ሰይፉ የቀድሞ የፖርላማ አባል ፤

ዶክተር ብሪ ያያ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ጉዳይ በቅርበት የሚከታተሉ የኅብረተሰብ ጉዳይ ምሁር ፤

ጋዜጠኛ ወልደጊዮርጊስ ገብረ ሕይወት የመቀሌ ዮንቨርስቲ የቀድሞ የዉጭ ጉዳይ ኃላፊ በአዲስ አበባ የሚገኝ የአንድ ሚዲያ ኃላፊ የነበረ እንዲሁም ፤

አቶ ቻላቸዉ ታደሰ ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ተንታኝ ናቸዉ።

ሙሉ ዉይይቱን የድምጽ ማድመጫ ማዕቀፉን በመቻን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን!

አዜብ ታደሰ

ሙሉ ዉይይቱን የድምጽ ማድመጫ ማዕቀፉን በመቻን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን!Audio Player00:0000:0000:00Use Up/Down Arrow keys to increase or decrease volume.