February 3, 2021

በትግራይ ክልል በሰላማዊ ዜጎች በደረሰው አደጋ ማዘኑን መንግስት ገለፀ

የመንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ዛሬ በሰጠው መግለጫ፦ ያለፈው ጥቅምት በተጀመረውና መንግሥት «የሕግ ማስከበር» ባለው ዘመቻ ወቅት በንፁሃን ዜጎች ለደረሰው ማንኛውም ጉዳት የኢትዮጵያ መንግስት ማዘኑን አስታውቋል።

መንግስት አያይዞም በዘመቻው ወቅት በአንድ ሰላማዊ ሰው ላይ የሚደርሰው ሞት እንኳ አሳዛኝ መሆኑን ገልፆ ሆኖም ዘመቻው በጥንቃቄ የተካሄደ በመሆኑ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች አልተጎዱም ማለቱን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ያሳያል።

በክልሉ የንፁሃን ዜጎችን ሞት በተመለከተ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የሚሰራጨው ዘገባም «ከእውነት የራቀና በመረጃ ያልተደገፈ» ነው ብሏል። የሞቱ ሰላማዊ ዜጎች ምን ያህል እንደሆኑ ግን ቁጥራቸውን ከመግለፅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያው ተቆጥቧል።መከላከያ በህግ ማስከበር ዘመቻው ወቅት በርካታ ንፁሃን ላይ አደጋ አድርሷል በሚል በዓለም አቀፉ መገናኛ ብዙኃን እየተሰረጨ ያለው መረጃ በማስረጃ ያልተደገፈና ከእውነት የራቀ ነው- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ

መከላከያ በህግ ማስከበር ዘመቻው ወቅት በርካታ ንፁሃን ላይ አደጋ አድርሷል በሚል በዓለም አቀፉ መገናኛ ብዙኃን እየተሰረጨ ያለው መረጃ በማስረጃ ያልተደገፈና ከእውነት የራቀ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል፡፡በህግ ማስከበር ዘመቻው ወቅት በአንድ ሰላማዊ ሰው ላይ እንኳን የሚደርስ አደጋ ብዙ መሆኑን ነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ የገለፀው፡፡

በህግ ማስከበር ዘመቻው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ንፁኃን ሰዎች ያልተጎዱት የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በዘመቻው ወቅት በታቀደና ወታደራዊ ሞያን ተግባራዊ በማድረጉ እንደሆነም ነው የተገለፀው፡፡

የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ የሚገኙ ኃይሎች ያልተሳካ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው አካላት እንደሆኑም የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ ጠቁሟል፡፡