FanaBC

Feb 3, 202186

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ካናዳ የነጭ የበላይነት የሚያቀነቅነውን ፕራውድ ቦይን በሽብርተኝነት ፈረጀች።

ካናዳ ይህን ቡድን ጨምራ አራት የቀኝ አክራሪ ቡድኖችን በሽብርተኝነት መፈረጇን በዛሬው ዕለት አስታውቃለች።

በዚህም አቶምዋፈን ዲቪዥን ፣ ቤዝ ፣ የሩሲያ ኢፔሪያል ንቅናቄን ጨምሮ 13 ቡድኖች በካናዳ የፌዴራል መንግስት በሽብርተኝነት ተፈርጀዋል።

በመሆኑም በሽብርተኝነት የተፈረጁት ቡድኖች በካናዳ መንቀሳቀስ የማይችሉ ሲሆን ንብረቶቻቸውም ሊወረሱ እንደሚችሉ ግሎባል ኒውዝ ዘግቧል።

የነጭ የበላይነት አቀንቃኙ ፕራውድ ቦይን ቀኝ አክራሪ እና ኒኦ ፋሽዝምን የሚያቀነቅን በአሜሪካ እና ካናዳ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው።

በቅርቡ በአሜሪካ ካፒቶል ሂል ከነበረው ሁከት ጋር በተያያዝ ስሙ ሲነሳ የነበረው ቡድኑ ለቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ድጋፍ እንዳለው ይነገራል።