February 4, 2021Konjit Sitotaw

አቶ ልደቱ አያሌው ለሕክምና ቀጠሮ ወደ አሜሪካ ለመብረር ተዘጋጅተው ከቦሌ ኤርፖርት በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች እንዲመለሱ መደረጉት የመረጃ ቲቪ ምንጮች አስታወቁ።

አቶ ልደቱ አያሌው ወደ አሜሪካ ለህክምና ባላቸው ቀጠሮ መሰረት ዛሬ ምሽት በረራ ለማድረግ ወደ ቦሌ ኤርፖርት የሔዱ ቢሆንም በመንግስት ሐይሎች መውጣት አይችሉም ተብለው ተመልሰዋል ሲል ምንጫችን ገልጿል።

አቶ ልደቱ አያሌው በእስር በነበሩበት ጊዜ ወደ አሜሪካ የህክምና ቀጠሮ እንዳላቸው ለፍርድ ቤት ሲያስረዱ እንደነበር ይታወሳል።