የእውነትን ሚዛን ከማዛባት የማይዋጥ መግለጫ ከመስጠት ዝም ማለት ይሻላል ! – ምንሊክ ሳልሳዊ

ካድሬዎች በሚመሩት ባለስልጣናት ንግግር ባደረጉበት ሰልፍ ሕዝብ በራሱ ፍላጎት ተሰልፏል ማለት፤ ሕዝብ በሕግ የተመዘገቡ ፓርቲዎችን በሰልፉ ፈርጇል ማለት ከፖለቲከኞች የሚጠበቅ ትልቅ ውሸት ነው። ሕዝብን ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀም ሊቆም ይገባል።
የኦሮሚያ ብልጽግና ለአብን አቤቱታና ለምርጫ ቦርድ መግለጫ መልስ ይሆነኛል ያለውን መግለጫ ሰጥቷል። ስማችን ተነሳ የሚሉ አካላት ህዝብ በዚህ ደረጃ ሊፈርጃቸው እንደቻለ በራሳቸው ሊመረምሩ ይገባል ሲሉ የኦሮሚያ ብልጽግና ባለስልጣን ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተሰምቷል። https://mereja.com/amharic/v2/451247
ከ90 በመቶ ያላነሰው የብልጽግና አባል ያው የድሮው የኢሕአዴግ አባል በመሆኑ፤ ይህ ሥልጣንን ለሀብት ምንጭ ያደረገ አካል ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ተቀባይነት በመጠቀም በለውጥ ስም በያዘው ሥልጣን ላይ ለመቀጠልና የምቾት ሕይወቱን ለመግፋት ባለ በሌለ አቅሙ እየተፍጨረጨረ እንደሆነ ያረጋገጠ ሰልፍ ነው፡፡ በሕዝብ ማሳበብ ጥላቻን ከማንገስ አይለይም።
ካድሬዎች በሚመሩት ባለስልጣናት ንግግር ባደረጉበት ሰልፍ ላይ ሕዝብ ህዝብ በራሱ ፍላጎት ተሰልፏል ማለት ሕዝብን እንደመናቅ ይቆጠራል። የደረጃው ያለው የዐቢይን አንጻራዊ ተቀባይነት በመጠቀም በሥልጣኑ ለመቀጠል የቋመጠ ካድሬ ያዘጋጀውና የመራው ሰልፍ እንደሆነ ጥርጥር የለውም፡፡ ይህ ሰልፍ የክልሉን ሕዝብ ስሜት በምንም ዓይነት ሊወክል እንደማይችል የሚያከራክር አይደለም፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ሰልፍ ደርግም ኢሕአዴግም እጥፍ ድርብ አድርገው በተደጋጋሚ አሳይተውናል፤ እናውቀዋለንና፡፡የማይመስል የማይዋጥ መግለጫ ከመስጣት ዝም ማለት ይሻላል። ሕዝብን ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀም ሊቆም ይገባል። #MinilikSalsawi
