Post published:February 5, 2021
ዘመን ተሻጋሪው ዲፕሎማት ፀሓፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድን የሚያክል ታላቅ ብልህና እጅግ አርቆ ተመልካች ዲፕሎማት ኢትዮጵያ አግኝታ አታውቅም-!!! ለእውቀት አልባው ታዬ ደንደአ የተሰጠ መልስ
* ወንድወሰን ተክሉ
*** ሀገራችንን ለአምስት አመታት ከ1928-1933 ድረስ የወረራት ፋሺስቱ ሞሶሎኒ መዘዝ ሀገራችንን ብዙ ዋጋ ያስከፈለ ተግዳሮትን የፈጠረ ነው::: በሁለተኛው የአለም ጦርነት ጣሊያን ጀርመን ሀንጋሪ ጃፓን በአንድ ወገን እንግሊዝ አሜሪካ ሶቪየት ህብረትና ፈረንሳይ በሌላ ወገን ሆነው ጦርነት ሲገጥሙ ከ1939-1945 እ ኤ አ በወቅቱ ጣሊያን ኢትዮጵያን ሊቢያን ሱማሊያን ወርሮ ነበርና እንግሊዝ ከስደተኛው ንጉሰነገስት ቀ.ኃ.ሥ ጋር ሆና ዘመተችበት:;
ጦርነቱ በአጭሩ ተጠናቆ ጣሊያን እንደተሸነፈ እንግሊዝ እግሯን በጣሊያን እግር ተክታ ኢትዮጵያን ለመግዛት የመገዝገዙን ስራ ሀ ብላ ጀመረች::: በተለይ ባህረ ነጋሽ የዛሬዋ ኤርትራ ከ1888 ጀምሮ በጣሊያን ስር ስለነበረች እንግሊዝ ሙሉ በሙሉ ሞግዚት ሆና መግዛት ስትጀምር ንጉሳዊው የኢትዮጵያ መንግስት አይደለም በኤርትራ ጉዳይ ውስጥ ተፅእኖን ለመፍጠር የሚያበቃ ሁኔታ ላይ መሆን ይቅርና ከመረብ ምላሽ መልስ ያለችዋንም ኢትዮጵያን በእንግሊዝ የበላይነት ስር እያስተዳደረ ያለ እጅግ ደካማና ሉአላዊነቱን ያልተቀዳጀ ያህል ተደፍቆ የነበረበት መጥፎ ጊዜ ነበር::
እናም ከእንግሊዝ 10ዓመት የሞግዚት አገዛዝነት በኃላ የኤርትራን እጣፈንታን ለመወሰን የተብይበሩት መንግስታት ድርጅት እንቅስቃሴ ሲጀምር የኢትዮጵያን መንግስት በመወከል ኒዮርክ ከትመው ሙግቱን የተያያዙት ብቸኛው ሰው ፀሃፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ናቸው:::
እንግዲህ ፀሃፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተወለድ በግርማዊነታቸው ቀ.ኃ.ሥ ንጉሰ ነገስት ዘ- ኢትዮጵያ ተወክለው ኤርትራን ወደ እናት ሀገራ ኢትዮጵያ ጋር ለማዋሀድ ተልእኮን ተቀብለው ወደ ኒዮርክ ባመሩበት ወቅት ክፍለሀገሪቱ ሙሉ በሙሉ በእንግሊዝ እጅ ስር የምትተዳደርበት ወቅት ከመሆኑም በላይ እንግሊዞች ደግሞ እራሳቸውን በጣሊያን እግር ተክተው ክፍለሀገሪቱን የመግዛት ካልሆነም ሙሉ ነፃነቷን በማቀዳጀት ከኢትዮጵያ ተገንጥላ ነፃ መንግስት የምትሆንበትን አቋም ይዘው የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው የኃይለስላሴ መንግስት ከክፍለሀገሪቱ ጋር እንዳችም አይነት ግንኙነት እንዳይኖረው በጥብቅ ያገዱበት ሁኔታ የነበረ ሲሆን በኒዮርክ ባለው የተመድ ፅ/ቤት ድምፅን በድምፅ የመሻር መብቱ ያላቸው ኃያላኑ 4 ሀገራት (አሜሪካ እንግሊዝ ፈረንሳይና ሶቪየት ህብረት ) የእንግሊዝን አቋም ደጋፊ የነበሩ በመሆናቸው ለፀሃፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ብቻቸውን ከእነዚህ ኃያላን ጋር ተሟግተው ኤርትራን ወደ እናት ሀገሯ ኢትዮጵያ እንዲያስመልሱ ተልእኮ ተሰጥቷቸው ነው ወደ ኒዮርክ መጏዝ የቻሉት:::
ተ መ ድ የኤርትራን ጉድይ የሚያጠና ኮሚቴ ሲያዋቅር የተመረጡት ሀገራት የኢጣሊያ የእንግሊዝና የአረብ ሀገራቱ አገር ወዳጆች ሆነው የመገኘታቸው ጉዳይ ደግሞ ሌላው እጅግ ፈታኙ የዲፕሎማሲ ትግል ነበር ለፀሃፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የገጠማቸው::
የሚገርመው አክሊሉ ረዳት አማካሪና መሰል ድጋፍ ስጪ ሉኡክ ሳይመደብላቸው ብቻቸውን እንዲሞግቱ የተመደቡ ሰው ሆነው ሳለ የተጣለባቸውን ታላቅ ሀገራዊ ኃላፊነትን ሌት ተቀን በመልፋትና በዲፕሎማሲው ኮሪደሮች ላይ በመፈላም አመታት ከፈጀው ትግላቸው በኃላ የእንግሊዝን የጣሊያንን የአረቦቹን ፍላጎትና ዲፕሎማሲያዊ ፍልሚያን ብቻቸውን አሸንፈው ተ መ ድ በኤርትራ ህዝበ ውሳኔ እንዲያካሂድ ማስወሰን የቻሉ ድንቅ ዲፕሎማት ናቸው::
የእንግሊዝ ፍላጎትና አላማ ኤርትራን በጣሊያን እግር ተክቶ መግዛት ወይም ካልሆነ ክፍለ ሀገሪቷን ነፃ ሀገር ማወጅ ሲሆን ጣሊያንና አረብ ሀገራቱም በተመሳሳይ ሁኔታ የኤርትራ አስተዳደር ወደ ጣሊያን እንዲመለስ አሊያም በእንግሊዝ እጅ እንድትገዛ ይህ ካልሆነ ግን ነፃነቷን ያወጀች ሀገር እንድትሆን ነበር እቅድና ፕላን አውጥተው ሲሞግቱ የነበረው::
ሆኖም ተ መ ድ የወጣቱንና አንደበተ ርቱኡን ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማትን አክሊሉ ሀብተወልድን አሳማኝ የመክእራከሪያ ነጥቦች ውድቅ ማድረጊያ ቀዳዳ በማጣቱ የኤርትራን እጣፈንታን እራሳቸው ኤርትራዊያን ይወስኑ በማለት ህዝበ ውሳኔ Referendum እንዲካሄድ ለመወሰን ተገደደ::
በተወሰነው ህዝበ ውሳኔ ላይም የኤርትራ ህዝብ- 👉
1ኛ – ነፃና ሉአላዊ መንግስት መፈለጉን
2ኛ – ከእብግሊዝ ጣሊያን አገዛዝ ስር ለመገዛት መፈለጉን
3ኛ – ከኢትዮጵያ ጋር 👉 በአንድነት 👉 በፌዴሬሽን/ኮንፌዴሬሽን መዋሃድ መፈለጉን በምርጫ እንዲመርጥ ቀርቦለት የኤርትራ ህዝብ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን ለመዋሃድ መፈለጉን በአብላጫ ድምፅ በመወሰኑ ኤርትራ ከስድስት አስርተ አመታት በኃላ ወደ እናት ሀገራ ኢትዮጵያ እንድትመለስ ያስቻሉት ብቸኛው ዲፕሎማት ፀሃፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ናቸው::
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሬፈረንደሙን በኤርትራ በሚያካሄድበት ወቅት ክፍለሀገሪቱ ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ መንግስት ቀጥተኛም ይሁን ተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት ታግዶ በእንግሊዝ የሞግዚት አገዛዝነት ስር ያለችበት ወቅ ሆኖ ሳለና የእንግሊዝ የጣሊያንና የአረቦቹ ሰፊ የቅስቀሳ ዘመቻ የተካሄደ ሆኖ ሳለ በአነሳባጋዲስ ኤርትራዊያን የአንድነት ኃይሎች ታላቅ ተጋድሎ ፅናትና መስዋእትነት ከኢትዮጵያ ጋር ለመዋሃድ የወሰኑበት ልዩና ታሪካዊ ክስተት ነበር የሪፈረንደሙ ሁኔታ::
አክሊሉ ሀብተወልድ ብቻቸውን ተሟግተው ኃያላኑን አሸንፈው ኤርትራን ወደ ኢትዮጵያ የመለሱ ታላቅ ዲፕሎማት ሲሆኑ ይህ በእሳቸው ጥረት የተገኘው የኤርትራ በፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር መዋሃድ ከአስር አመት በኃላ በኤርትራው ሀገረ ገዢ እንደራሴ ልጅ ተድላ ባይሩ ይእሚመራው የኤርትራዊያን የአንድነት ኃይሎች ታላቅ ተጋድሎና ተፅእና ንጉሰ ነገስቱ ቀ.ኃ.ሥ የፀሃፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድን የፌዴሬሽኑን እንድያፈርሱ ውትወታና ተማፅኖን ችላ በማለት የእነተድላ ባይሩን ሀሳብ ተቀብለው በማስተናገድ የፌዴሬሽኑን መፍረስ ለማወጅ ቻሉ::
አክሊሉ ሀብተወልድ የእነተድላ ብይሩን ውትወታ ንጉሱ ጃንሆይ እንዳይቀበሉና ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን መኖር ወደ ኃላ ላይ እነጅቡቲን ሱማሌን የምንመልስበት ተምሳሌት ይሆናል እያሉ ሲሞግቱና ሲከላከሉ የነበረበትን ታሪክ የማያውቁት እንደነ ታዬደንደአ ተብዬ ደደብ ካድሬ አክሊሉ ሀብተወልድ የኤርትራን ፌዴሬሽንን በማፍረስ የኢትዮጵያ ጠላት ናቸው ብሎ ሲናገር መስማትም ሆነ ማንበብ ስለሚያንገሸግሽ ነው ይህንን ታሪክ ቀመስ መጣጥፍን ለታዬ ደንደአ ተብዬው እውቀት አልባ መልስ ለመፃፍ የቻልኩት;: