February 8, 2021

አዲስ አበባን የማውደምእንቅስቃሴ ይቁም! – ባልደራስ

አዲስ አበባ እቴጌ መነን ትምህርት ቤት አጠገብ የሚገኘው የደጃዝማት አስፋው ከበደ ቤት የነበረ ቅርስ በኦሕዴድ/ብልፅግና ፈርሷል:: በምትኩም የኦሕዴድ ወታደራዊ ካምፕ እንደሚሠራበት ተነግሯል::

ይህም በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተነገረው ከተማዋን በስውር የማውደም ስትራቴጂ አካል ነው:: ታሪክ እያጠፉ የወታደር ጎጆ መቀለስ ሀገር አውዳሚነት ነው:: ፀረ ኢትዮጵዊነት ነው:: አሁንም ቅርሱ ታድሶ ወደነበረበት ገፅታ ሊመለስ ይገባል:: አፍራሾች የአዲስ አበባን ሕዝብ በይፋ ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል:: ሕዝቡም ይህ እንዲሆን መጠየቅ አለበት::

ይህንን የማድረግ ሚናው የደጃዝማች አስፋው ቤተሰቦች ብቻ መሆን የለበትም:: ተረኛው ኦሕዴድ/ብልፅግና ሀገር አውዳሚነቱን በአስቸኳይ ሊያቆም ይገባል:: አዲስ አበባ የኦሕዴድ እስር ቤት አትሆንም::

የሕወሓት ልዩ ጥቅም ማዕከል የነበሩት ከአማራ የነጠቃቸው ራያና ወልቃይት ነበሩ:: የኦሕዴድ ደግሞ አዲስ አበባ ሆናለች:: አሁን ከልዩ ጥቅምም ታልፎ ከተማዋን የማጥፋት ተግባር ነው የተያዘው:: በመሆኑም የአዲስ አበባ ሕዝብ ብሎም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አባቶቹ በገነቧት ከተማ ፍርስራሽ ላይ ለመቆም መፍቀድ የለበትም::